Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤትና የመንገዶች ባለሥልጣን ቡድን መሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በታሰሩት፣ በሃዚ አይአይ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤትና በባለሥልጣኑ ዕቃ አቅርቦት ቡድን መሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

የኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዛኪር አህመድና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኮንስትራክሽን ዕቃ አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ካሳዬ ካቺ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ሐሙስ ነሐሴ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ነው፡፡

ቡድን መሪው ከአራት ዓመት በፊት ለሳትኮምና ለሃዚ አይአይ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ከመካኒሳ እስከ ዓለም ገና ለሚሠራው የመንገድ ግንባታ 500 በርሜል ሬንጅ (አስፋልት) በውሰት መስጠታቸውን፣ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ድርጅቶቹ የተዋሱትን አስፋልት በሦስት ወራት ውስጥ መመለስ ሲገባቸው ከቡድን መሪው ጋር በመመሳጠር ሳይመልሱ በመቅረታቸው፣ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱንም መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ በተሰጠው የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የስምንት ሰዎች የምስክርነት ቃልና የተጠርጣሪዎቹን ቃል መቀበሉን፣ እንዲሁም ንብረታቸውን ማገዱን ገልጿል፡፡ ቀሪ የሰባት ምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ ሰነዶችን ለመሰብሰብና የቴክኒክ ሥራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች የመርማሪ ቡድኑን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ተቃውመዋል፡፡ ማስረጃዎቹን መርማሪ ቡድኑ ወስዶ መጨረሱን ገልጸዋል፡፡ ሰነዶቹም በመንግሥት ተቋም የሚገኙ በመሆናቸው፣ ደንበኞቻቸው መታሰር ስለሌለባቸው የዋስ መብታቸው እንዲፈቀድላቸውና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ግን ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካሰማ በኋላ የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፣ ለመርማሪ ቡድኑ አሥር ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ ለነሐሴ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች