Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዋልያዎቹ አሠልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ

የዋልያዎቹ አሠልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና አቻው ጋር ካካሄደ በኋላ ብዙ ትችትና ችግር እየተነሳባቸው ያሉት ዋና አሠልጣኙ አሸናፊ በቀለ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ፡፡   

ብሔራዊ ቡድኑ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ኬንያ ለምታስተናግደው የቻን ውድድር በሐዋሳ ስታዲየም ጎረቤቷን ሱዳንን ገጥሞ 1ለ1 በሆነ ውጤትም መለያየቱ ይታወሳል፡፡ ማተሚያ ቤት ቀድመን በመግባታችን ውጤቱን አልያዝም እንጂ የመልስ ጨዋታውን ቅዳሜ ነሐሴ 13 ቀን አከናውኗል፡፡

በመጀመርያው ጨዋታ በእንግዳው ቡድን ቅድሚያ የተቆጠረበት ብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኙ የተከተሉት የጨዋታ ዘይቤና ቡድኑ ላይ ሲታይ የነበረው ተነሳሽነትና ወቅታዊ አቅም ቅሬታ ማስነሳቱ ተጠቅሷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለን በአሠልጣኝነት ከሾመ በኋላ ከጋና፣ ከጂቡቲና ከሱዳን ጋር ጨዋታ ያደረገ ሲሆን፣ ቡድኑ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩት ችግሮች ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ትኩረት ማጣትና በአሠልጣኙ ውሳኔ ላይ እየተደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት ዋነኛው የችግሩ ማሳያ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

አዲስ አሠልጣኝ ከተሾመ በኋላ አሠልጣኙ ተጫዋቾች የሚመረጡበትና የሚቀላቀሉበት መንገድ፣ ለቡድኑ የሚያስፈልገውን ማቴሪያል ከማቅረብ አንፃር ችግር እየገጠመ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከቻኑ ማጣሪያ ጨዋታ በኋላ ቡድኑን እንደሚለቁና የመልቀቂያ ደብዳቤ እንዳስገቡ የአሠልጣኙ የቅርብ ሰዎች ተናግረዋል፡፡  

አሠልጣኙ በማጣሪያ ጨዋታ አነስተኛ ተጫዋቾች በመያዝ መዘጋጀታቸው፣ ጋዜጣዊ መግለጫ ለጋዜጠኞች አለመስጠትና በተጨዋቾች ምርጫ ላይ የፌዴሬሽኑ ጣልቃ ገብነት የቡድኑ ከበፊቱ አቋም እያሽቆለቆለ መምጣቱ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ የስፖርት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

በሐዋሳ ከሱዳን ጋር የማጣሪያ ጨዋታ ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ አማካይ ቦታ ላይ ሲስተዋል የነበረው ችግሩ ምን ያክል ሥር እየሰደደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአሠልጣኙ መልቀቂያ ማስገባታቸው ከተሰማ በኋላ የቀድሞ ክለባቸው አዳማ ከተማ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ እየተጠቆመ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2019 በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ያደረገው  ብሔራዊ ቡድኑ በጋናው ጨዋታ ሽንፈት ማስተናዱ ይታወሳል፡፡ የዕለቱን የ5ለ0 ሽንፈት በተመለከተም ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ቡድኑ በጋናው ጨዋታ የነበሩበትን ጉልህ ስህተቶችና ክፍተቶች አርሞ ለቀጣይ ግጥሚያዎች የተሻለ ቡድን ሆኖ እንደሚቀርብ ያመለከተበት ሪፖርት አካቶ ነበር፡፡ ለዚያም በቂ የዝግጅት ጊዜና የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያስፈልጉ ቢጠቀስም ከዛምቢያ አቻው ጋር ብቻ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ለሚከናወነው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ ከጋና፣ ከኬንያና ሴራሊዮን ጋር የተደለደለው ብሔራዊ ቡድን አምስት ቀሪ የምድብ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሲሆን፣ በቀጣይ ለሚያደርገው ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባው እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በተለያዩ ጨዋታዎች የተለያዩ አሠልጣኞችን በመቀየር የሚታወቀው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የወራት ዕድሜ ያላቸውን አሠልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ችግሩን የበለጠ እያሰፋው እንደሚመጣ አስተያየታቸውን  የሚሰነዝሩ አካላት አልጠፉም፡፡

በመጋቢት 2010 ዓ.ም. ሁለተኛ የአፍሪካ ማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድን በቂ ዝግጅት አድርጎ ለውድድር መቅረብ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል፡፡

ፌዴሬሽኑ የተወሰኑ ችግሮች እንዳሉበት ቢጠቁምም በሒደት ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠራ ገልጿል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታና የተጫዋች አመራረጥን በተመለከተ ጣልቃ ገብነት ካለባቸው አሠልጣኙ ለሚመርጡት አጨዋወት ይመጥናሉ የሚሏቸውን ተጫዋች የመምረጥ ሙሉ መብት እንዳላቸው ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...