Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየወፎች ዝማሬና ተጓዳኝ ፍለጋ

የወፎች ዝማሬና ተጓዳኝ ፍለጋ

ቀን:

የወፎች ዝማሬ በድንገት ትኩረትህን ስቦት ያውቃል? የተለያዩ ዜማዎችን በማሰማት ችሎታቸው አልተደነቅህም? ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዝማሬ የሚያሰሙት አንተን ለማዝናናት ብለው እንዳልሆነ ታውቃለህ? መዝሙሮቻቸው አስፈላጊ የሆኑ መልእክቶችን የሚያስተላልፉባቸው ዘዴዎች ናቸው። ክልላቸውን ለማስከበር ሲሉ ዝማሬ የሚያሰሙበት ጊዜ ቢኖሩም አብዛኛውን ጊዜ ግን የሚዘምሩት ተጓዳኝ ለመሳብ ሲሉ ነው።  ኒው ቡክ ኦቭ ኖውሌጅ እንደሚለው ወንዱና ሴቷ አንዴ ከተገናኙ በኋላ “የመዝሙሩ መጠን እስከ 90 በመቶ ድረስ ይቀንሳል።”

ይሁን እንጂ ተጓዳኝ ለመማረክ ጥሩ መዝሙር ብቻ በቂ የማይሆንበት ጊዜ አለ። አንዳንድ እንስት ወፎች በተባዕቱ ከመሸነፋቸው በፊት “ጥሎሽ” እንዲጣልላቸው ይፈልጋሉ። ስለዚህ ዊቨርበርድ የተባለው ወፍ በጥያቄው ከመግፋቱ በፊት ጎጆ የመሥራት ችሎታውን ማስመስከር ይኖርበታል። ሌሎች ተባዕት የአእዋፍ ዝርያዎች ደግሞ እንስቷን ቃል በቃል በመቀለብ ለቤተሰባቸው መተዳደሪያ የማቅረብ ችሎታቸውን ማስመስከር ይኖርባቸዋል።

ጄደብሊው ዶትኦርግ በድረ ገጹ እንደጻፈው፣ እንስሳት ሐሳብ ለሐሳብ የሚግባቡባቸው መንገዶች አካላዊ ፍላጎቶቻቸውን ከማሟላት አልፈው ብዙ ጠብ እንዳይፈጠር በማድረግ በዱር ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋሉ። በእንስሳት የሐሳብ ልውውጥ ላይ የሚደረገው ምርምር እየቀጠለ በሄደ መጠን ስለ “ዱር አራዊት ጭውውት” የምናውቀው ብዙ ነገር ይኖረናል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ