Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበሰቨን ናይን ኤይት ጋለሪዎች፣ የመጻሕፍት መደብሮች፣ ሬስቶራንቶችና ሌሎችም የጥበብና ባህል ማዕከሎች ያሉ...

በሰቨን ናይን ኤይት ጋለሪዎች፣ የመጻሕፍት መደብሮች፣ ሬስቶራንቶችና ሌሎችም የጥበብና ባህል ማዕከሎች ያሉ ሲሆን፣ ከ75 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ጎብኝተውታል

ቀን:

በሰቨን ናይን ኤይት ጋለሪዎች፣ የመጻሕፍት መደብሮች፣ ሬስቶራንቶችና ሌሎችም የጥበብና ባህል ማዕከሎች ያሉ ሲሆን፣ ከ75 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ጎብኝተውታል

ምስጋና
ተመስገን ፈጣሪያችን!
እንደፈሪነታችን፣
ወጥተን እንድንገባ፣ ብርሀን እንድናይ የፈቀደ፤
ያስቀመጥካትን ጸሀይ፣ ከሰማይ ያላወረደ፤
እሩህሩህ ገዢ የሰጠኸን፤
ፈጣሪያችን ተመስገን፡፡
እንደሆዳምነታችን፣
ለእለት ቀለብ የሚነዳን እንጂ፤
በእለት ቀለብ የሚቀጣን፤
ገዢ ያልሰጠኸን፣
ፈጣሪያችን ተመስገን፡፡
እንደበደል መቻላችን፣
ለጥይቱ ዋጋ የሚጨነቅ፣
ደርሶ ገዳይ ገዢ ያልሰጠኸን፤
ፈጣሪያችን ተመስገን!!
ገዢያችንም ተመስገን!!
እንደፍርሀታችን፣
ኮርቻ ጭነህ ያልጋለብከን፤
እንደሆዳምነታችን፣
ሰብእናችንን ገፈህ፣ ከከብት ጋጣ ያላኖርከን፤
እንደተገዢነታችን፣
የጸሎት ቤታችንን ንደህ፣ መመለኪያህን ያላቆምክ፤
እንደአለመጠየቃችን፣
እንበላበት ዘንድ ፈቅደህ፣ አፋችንን ያለጎምክ፤
ተመስገን!!
 – በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) ‹‹የተስፋ ክትባት›› (2008)

 

***

በኩኩሉ ጨዋታ በልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ የተደበቀ ሕፃን

ሕፃናት ሲጫወቱ ስለመጫወታቸው እንጂ በጨዋታ ወቅት የሚፈጽሙት ድርጊት ጉዳት ስለማስከተሉ ብዙም አያስተውሉም፡፡ በሰሜናዊ ዩክሬን ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖር የሰባት ዓመት ታዳጊ ሕፃን ያጋጠመውም በጨዋታ ወቅት ራሱን ለመደበቅ ከገባበት የልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ እንደአገባቡ መውጣት አለመቻሉ ነው፡፡

ከእህቱ ጋር ኩኩሉ እየተጫወተ በነበረበት ወNት ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ጭንቅላቱን አስቀድሞ የገባውን ሕፃን፣ ቤተሰቦቹ ከማሽን ለማውጣት ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች መጥራትም ግድ ነበር፡፡ አራት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ተሰማርተው ሕፃኑን ያለጉዳት ከማሽኑ አውጥተውታል፡፡ ሜትሮ ዩኬ ሕፃኑ ማሽኑ ውስጥ በቆየበት ጊዜ አለማልቀሱን አስፍሯል፡፡

***

የፖሊስ ፈረስ ለመምታት የቃጣ ግለሰብ ታሰረ

በአገራችን እንስሳትን መደብደብ የተለመደ ነው፡፡ ሰውንም ቢሆን እንዲሁ፡፡ የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ባሉበትና በሠለጠነው ዓለም ግን መማታት አጥብቆ የተከለከለና በሕግ ሚያስቀጣም ነው፡፡ ማኅበረሰቡም መማታትን የሚደግፍ አይደለም፡፡ ይኼንን የማኅበረሰብ እሴት የጣሰ የማሳቹሰትስ ነዋሪ ግን የፖሊስ ፈረስ ፊት ላይ እጁን በመሰንዘሩ ለእስር ተዳርጓል፡፡ ሮይተርስ እንዳለው፣ የ59 ዓመቱ ዶናልድ ፓጋን ፖሊስ ያፈናጠጠውን ፈረስ የተተናኮሰው በከተማዋ ጎዳና የቢራ ፌስቲቫል በሚካሄድበት ወቅት ነበር፡፡ የፈረሱን ፊት በጡጫ ሊመታ ሲል ፈረሱ ራሱን ለመከላከል የፊት እግሩን አንስቶ በመቆሙ የተፈናጠጠው ፖሊስ ተጎድቷል በሚል ፓጋን ለእስር ተዳርጓል፡፡

***

ከ10 ሺሕ እንቁላሎች የተሠራ ኦምሌት

በቤልጂየም ለዶሮዎች በሚዘጋጅ ምግብ ውስጥ በሚገባ ኬሚካል ምክንያት እንቁላል ተመርዟል በሚል በሕዝቡ ውስጥ የነገሠውን ፍርሃት ለማስወገድ ከ10ሺሕ እንቁላሎች የተሠራ ኦምሌት ሰሞኑን ተዘጋጅቶ ነበር፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው፣ 10ሺሕ እንቁላሎቹ የተጠበሱት አራት ሜትር ስፋት ባለው ድስት ውስጥ ሲሆን፣ የተጠቀሙት ማብሰያም ማገዶ ነው፡፡

የአውሮፓን ደረጃ የማያሟሉ ምግቦችን ዶሮዎች ተመግበዋል በሚል በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንቁላሎች ከአውሮፓ ሱፐርማርኬቶች እንዲወገዱ የተደረገ ሲሆን፣ የቤልጂየሙ የእንቁላል ግግር የተዘጋጀውም፣ በሕዝቡ ውስጥ የነገሠውን ፍርሃት ለማስወድ ነው ተብሏል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት የተዘጋጀው እንቁላል ጤናማ መሆኑም ተገልጿል፡፡

***

በደቡብ ዋልታ 100 ዓመት ያስቆጠረ ኬክ ተገኘ

መቶ ዓመት አስቆጥሯል የተባለ የፍራፍሬ ኬክ (ፍሩት ኬክ) በአንታርክቲካ በሚገኝ ሕንፃ ውስጥ ተገኘ፡፡ ኬኩ የተገኘው ከብረት በተሠራ ሳጥን ውስጥ ሲሆን፣ ሳጥኑም ዝጎና ተሰነጣጥቆ ነበር፡፡ ሆኖም በውስጥ ያለው ኬክ ለዓይን የሚስብ ሽታውም ትኩስ እንደሚበላ ኬክ ነበር፡፡

የአንታርክቲክ ሄሪቴጅ ትረስት እንዳለው፣ ኬኩና የታሸገበት የብረት ማስቀመጫ ለላቦራቶሪ ምርምር ኒውዚላንድ ወደሚገኘው ሙዚየም ተወስዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...