የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከጃፓኑ ዓለም አቀፍ የስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ነሐሴ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ተፈራርሟል፡፡ ፌዴሬሽኑ ስምምነቱ በስፖርት ሳይንስ ዘርፎች በተለይ በብቃት ምዘናና ትንተና በስፖርት ሕክምና፣ በስፖርት ሥነ ምግብ፣ በሥነልቦና፣ በአትሌቲክስ ሥልጠና እንዲሁም በሴቶች አትሌቶች ጉዳይ ለመሥራት ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ ስምምነቱን የተፈራረሙት ፌዴሬሽኑን በመወከል ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ (ፎቶ በቀኝ) እና የጃፓኑ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶ/ር ሄዴኪ ናቸው፡፡