Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለሕዝብና ቤት ቆጠራ የተገዙ ኮምፒዩተሮችና ፓወር ባንኮች እስካሁን አልቀረቡም

ለሕዝብና ቤት ቆጠራ የተገዙ ኮምፒዩተሮችና ፓወር ባንኮች እስካሁን አልቀረቡም

ቀን:

  የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በሚቀጥለው ዓመት ለሚያከናውነው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ የተገዙ 180 ሺሕ ታብሌት ኮምፒዩተሮችና 126 ሺሕ ፓወር ባንኮች እስካሁን አልቀረቡም፡፡ ኤጀንሲው በአንድ ወር ውስጥ እንዲቀርቡለት ጠይቋል፡፡

      በሐምሌ ወር በተደረገ የኮንትራት ውል ሌኖቮና ህዋዌ የተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕቃዎች አምራች ድርጀቶች፣ በ665 ሚሊዮን ብር ክፍያ ዕቃዎችን እንዲያቀርቡ መታዘዙ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ሁለቱ ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው 90 ሺሕ ኮምፒዩተር ታብሌቶችን፣ እንዲሁም ፓወር ባንኮችን በተመለከተም እያንዳንዳቸው 36 ሺሕ እንዲያቀርቡ ተብሎ ነበር፡፡

ዕቃዎቹን እያመረቱ ከሥር ከሥር እንዲያቀርቡና በሦስት ወራት ውስጥ እንዲያጠናቅቁ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡

ነገር ግን እስካሁን አንዳቸውም ኩባንያዎች የመጀመርያውን ዙር አቅርቦት እንኳን እንዳልጀመሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኅዳር 2010 ዓ.ም. የሚደረገው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉለት የቆዩ ሲሆን፣ ይህ ግዥ በነበረው የተጫራቾች እሰጥ አገባና ቅሬታ ምክንያት ከተጠበቀው በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡

ጨረታው መጀመርያ ሲጀመር ዕቃዎቹ በግንቦት 2009 ዓ.ም. ይቀርባሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

‹‹ከሁለቱ ኩባንያዎች የሚቀርቡት ዕቃዎች ቢያንስ የመጀመርያው ዙርና አብዛኛው አቅርቦት መስከረም ላይ እንዲመጣ ጫና እየፈጠርን ነው፤›› ሲሉ፣ የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሰልፌው አበራ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ወደ ሦስት ቢሊዮን ብር ተበጅቶለት እየተከናወነ ያለው የሕዝብ የቤቶች ቆጠራ ዝግጅት፣ ወደ 40 በመቶ የሚሆነው ወጪ በለጋሾች የሚሸፈን ነው፡፡

‹‹በቅርቡ አጠቃላይ ዝግጅቶቹንና ቀጣይ ሥራዎችን ይፋ እናደርጋለን፤›› ሲሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...