Sunday, May 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በቅርቡ ከቻይና ለተገኙ ብድሮች የክፍያ ማስተማመኛ ዝግ ሒሳብ በውጭ ባንኮች ሊከፈት ነው

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ ከወራት በፊት ከቻይና መንግሥት ላገኘቻቸው ሁለት ብድሮች የክፍያ ማስተማመኛ ዝግ ሒሳብ በውጭ ባንኮች ልትከፍት ነው፡፡ ብድሮቹ የተገኙት ከቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ ነው፡፡ የመጀመርያው ብድር የሚውለው ለሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የአርሲ ነገሌ-ሐዋሳ ፕሮጀክት ግንባታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ለአዳማ ሁናን የማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዞን ግንባታ ማስፈጸሚያ እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ለአርሲ ነገሌ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ የቻይና መንግሥት 171.08 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሲያቀርብ፣ ለአዳማ ሁናን የኢንዱስትሪ ዞን ደግሞ 262.3 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተገኝቷል፡፡

እነዚህ ሁለት ብድሮች ለመመለሳቸው ማስተማመኛ ‹ኤስክሮው አካውንት› እንዲከፍት ግዴታ ውስጥ መግባቱን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

‹ኤስክሮው አካውንት› ማለት ብድሩን የተዋዋሉት ወገኖች በሦስተኛ ወገን ባንክ ውስጥ የሚከፈት ዝግ የባንክ ሒሳብ መሆኑ ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት ከቻይና ላገኛቸው ሁለት ብድሮች በድምሩ 433.3 ሚሊዮን ዶላር ብድር፣ ሁለት ዝግ ሒሳቦችን መክፈት እንደሚጠበቅበት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በተገባው ስምምነት መሠረት በብድሩ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ሥራ ሲጀምሩ የሚያመነጩት ገቢ በቀጥታ ወደዚህ ዝግ የባንክ ሒሳብ ተቀማጭ በመሆን ለአበዳሪው መተማመኛነት ውሎ፣ በመጨረሻም ተከፋይ ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ኤስክሮው አካውንት አበዳሪዎች ብድራቸው እንደሚመለስ እርግጠኛ የሚሆኑበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑም ታውቋል፡፡

ለሁለቱ ብድሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት በመቶ ወለድ የሚከፍል ስለሆነ፣ ዕዳው በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች