Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊኢሠማኮ የአሠሪና ሠራተኛ ረቂቅ አዋጅ አሳስቦኛል አለ

  ኢሠማኮ የአሠሪና ሠራተኛ ረቂቅ አዋጅ አሳስቦኛል አለ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በአሠሪና ሠራተኛ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ የተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች አሳስበውኛል አለ፡፡ በረቂቁ ልዩነት አለኝ ባላቸው አንቀጾች ላይ ከሠራተኛ ማኅበራት ጋር በመምከር አቋሙን ለመንግሥት ለማሳወቅ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡  

  ለዓመታት ሲንከባለልና የተለያዩ ማሻሻያዎች ሲካተቱበት የቆየው ይህ ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ዓመት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ቢሆንም፣ የሠራተኞችን መብት ሊያስጠብቁ አይችሉም የተባሉ አንዳንድ አንቀጾችን ኢሠማኮ እንደሚቃወም ገልጿል፡፡

  ከኢሠማኮ የተገኘው መረጃ እንደማያስረዳው፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ልዩነት የታየባቸው አንቀጾች ላይ ከሠራተኞች ጋር በመምከር ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ብሎ ያመነባቸው ስምንት አንቀጾችን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለማቅረብ አቅዷል፡፡

  ‹‹ረቂቅ አዋጁ ላይ ለአምስት ዓመታት ስንደራደርበት ቆይተናል፤›› ያሉት የኢሠማኮ ፕሬዚንት አቶ ካሣሁን ፎሎ፣ ይህ ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ዓመት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢቀርብም መወያየት ያለባቸው ባለድርሻ አካላት በደንብ አልተወያዩበትም ነበር ብለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለባለድርሻ አካላት መመለሱን አስታውሰዋል፡፡ ‹‹ከተመለሰ በኋላ ግን በሦስትዮሽ የተወያይተንባቸው ነጥቦች ተቀይረው፣ እንዲያውም ያልተወያየንባቸው አንቀጾች ተጨምረው አዲስ ረቂቅ ሆኖ ወጥቷል፤›› ብለዋል፡፡  

  አዲስ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም፣ ምንም ዓይነት መሻሻል ሳይደረግበትና በሠራተኞች ማኅበር በኩል የቀረበው ማሻሻያ ሳይካተትበት የተቀረፀ ረቂቅ እንደሆነባቸው አቶ ካሣሁን አስረድተዋል፡፡

  ኢሠማኮ በስምንት አንቀጾች ላይ ልዩነት እንዳለው የጠቆሙት አቶ ካሣሁን ‹‹እነዚህ አንቀጾች በተግባር ላይ ቢውሉ የተረጋጋ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዳይፈጠር የሚያደርጉና የሠራተኛውን መብት የሚጥሱ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

  የኢሠማኮን አቋም ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡ በቅርቡ ከሠራተኛ ማኅበራት መሪዎች ጋር ተወያይተው በረቂቁ አዋጁ ውስጥ በማይስማሙባቸው አንቀጾች ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡ ‹‹የሠራተኛው መሪዎች ለውይይት ያቀረብናቸውን አንቀጾች ተቀበሉ ካሉን እንቀበላለን፡፡ ልዩነት አለን ካሉ ደግሞ ልዩነቱን ይዘን እንቀጥላለን፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

  ልዩነት የተፈጠረባቸውን አንቀጾች ለጊዜው ከመግለጽ የተቆጠቡት አቶ ካሣሁን፣ ከማኅበራት መሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ይፋ እንደሚያደርጉና በሚገኘው ምላሽ መሠረትም ኢሠማኮ አቋም እንደሚይዝ አመልክተዋል፡፡

  በረቂቅ አዋጁ በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ቁጥር 377/96 የተካተቱና ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ካስቀመጣቸው ውስጥ የሠራተኞች የዕረፍት ጊዜ፣ የዓመት ፈቃድ አሠጣጥ፣ ለሥራ ስንብት የተቀመጠው የጊዜ ገደብ፣ የኤጀንት ሥራ ቀጣሪዎች ጉዳይ፣ የሥራ የሙከራ ጊዜ፣ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጥ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡  

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...