Thursday, May 23, 2024

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሥራ ላይ የሚገኙ አምስት አምባሳደሮችን ጠራ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሥራ ላይ የሚገኙ አምስት አምባሳደሮችን መጥራቱን የሪፖርተር ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ።

ወደ አገር በተጠሩት አምባሳደሮች ምትክም ሰሞኑን በአገሪቱ ፕሬዚዳንት የአምባሳደርነትና የልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ያገኙት የቀድሞ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ አመራሮች ይመደባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወደ አገር እንዲመለሱ ጥሪ ከተደረገላቸው አምባሳደሮች መካከል በቻይና የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ሥዩም መስፍን፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ፣ በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ተሾመ ቶጋ፣ በፈረንሣይ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ነጋ ፀጋዬ፣ እንዲሁም በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ ገና አንድ ዓመት እንኳን ያልሞላቸው አቶ ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

 ፕሬዚዳንት ሙላቱ ሐምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት የባለሙሉ አምባሳደርነት ሹመት 11 የቀድሞ አመራሮች መሾማቸውን መዘገቡ ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ሰሞኑን ከሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ ካሣ ተክለ ብርሃንና  ሽፈራው ተክለ ማሪያም ዶ/ር ይገኙበታል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና፣ አቶ አሊ ሱሌይማን፣ ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ፣ አምባሳደር ተበጀ በርሄ፣ አቶ መታሰቢያ ታደሰ፣ አቶ ሙሉጌታ ዘውዴና ወ/ሮ ሉሊት ዘውዴ ተጠቃሽ ናቸው። በአምባሳደርነት የተሾሙት ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -