Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሐዋሳና ኤሌክትሪክ ተጫዋቾች ጨዋታ ለማጭበርበር መሞከራቸው ተረጋገጠ

የሐዋሳና ኤሌክትሪክ ተጫዋቾች ጨዋታ ለማጭበርበር መሞከራቸው ተረጋገጠ

ቀን:

የሐዋሳና ኤሌክትሪክ ክለቦች ባደረጉት የ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የክለቦቹ ተጫዋቾች ጨዋታ ለማጭበርበር መሞከራቸው ተረጋገጠ፡፡

ሰኔ 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ በተካሄደው የ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ውጤት ለማስቀየር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ተጫዋቾች እንደነበሩ ማረጋገጡን ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው አጣሪ ኮሚቴ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ሐሙስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በጋዜጣዊ መግለጫ ሪፖርቱን ያቀረበው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጣሪ ቡድኑ በጉዳዩ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጫዋቾችን ይፋ አድርጓል፡፡

ወሬው ከተሰማ በኋላ ፌዴሬሽኑ ሁለት አባላት ያሉበት አጣሪ ኮሚቴ በማዋቀር የ20 ቀናት ማጣራት ያደረገ ሲሆን፣ የጨዋታ ውጤት አስቀይረዋል ተብሎ የተጠረጠረው የሐዋሳ ከነማ ተጫዋች ኤፍሬም ዘካሪያስ በጉዳዩ ውስጥ እጁ እንደሌለበት አጣርቻለሁ ብሏል፡፡

በአንፃሩ ግን ተጫዋቹ ጨዋታ ለማጭበርበር ሲንቀሳቀስ አግኝቸዋለሁ ብሎ ክለቡ ሐዋሳ ከተማ ለፌዴሬሽኑ ቅጣት እንዲወስንበት በደብዳቤ ያቀረበ ቢሆንም፣ አጣሪ ኮሚቴው ግን ከኤፍሬም ዘካሪያስ ጋር ምንም ዓይነት የወንጀል ክስ እንዳላቀረበበትና ክለቡ ያስተላለፈበት የ25  ሺሕ ብር ቅጣትም በክለቡ ውስጥ ባሳየው ያልተገባ ተግባር እንደተቀጣ መግለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ኮሚቴ አባል ኢንስፔክተር ጌታቸው የማነ ብርሃን ገልጸዋል፡፡

የሐዋሳ እግር ኳስ ክለብ ጨዋታ ከመከናወኑ አምስት ቀናት በፊት ተጫዋቾቹ ከኤሌክትሪክ ተጫዋቾች ጋር እየተደራደሩ መሆኑን ሰምቶ ስብሰባ በመጥራት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቁን ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው የማነ ብርሃን አስረድተዋል፡፡

ከተጫዋቾቹ ጋር በተደረገው ስብሰባ ወቅትም ተጫዋቾቹ በልምምድ ቦታ ላይ የተጎዱ መስለው ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ፣ በጉዳትም ምክንያት ጨዋታው ላይ እንዳይገኙ እንዲሁም ወደ ጨዋታው ከገቡ በኋላ የተጎዱ መስለው ጨዋታቸውን አቋርጠው እንዲወጡ የሚል ማግባቢያ አድርገው እንደነበረ ተጠቅሷል፡፡

ሙከራው መከሰቱን ተከትሎም ከተጨዋቾቹ ጋር የተወያየው ክለቡ ጥብቅ ቁጥጥር በተጫዋቾቹ ላይ ለማድረግ መወሰኑን የአጣሪ ኮሚቴው በሪፖርቱ ሒደቱን አስታውሷል፡፡

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ውስጥ ግን የኤፍሬም ዘካሪያስ ስም አለመኖሩን ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ክለቡ ከፖሊስ ኮሚሽንና የደኅንነት ቢሮ ጋር በመሆን ማጣራት እንዳደረገ ያብራራው የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት፣ ኤፍሬም ከኤሌክትሪክ ተጫዋቾች ጋር በግል ጉዳይ ምክንያት ብቻ እንደተደዋወለ ማስረዳቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም በ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ጅማ አባቡና እግር ኳስ ክለብ ለፌዴሬሽኑ ይጣራልኝ የሚል መከራከሪያ ሐሳብ ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክና የሐዋሳ ተጫዋቾች በስልክ የተለዋጡትን መልዕክት ከኢትዮ ቴሌኮም ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት የኤሌክትሪክ ተጫዋቾች የሆኑት ዳዊት እስጢፋኖስ፣ ፍጹም ገብረ እግዚአብሔርና ሙሉዓለም ጥላሁን ከሐዋሳው ኤፍሬም ዘካሪያስ ጋር መነጋገራቸውን የሚያሳይ መረጃ አቅርቧል፡፡

መረጃውን በተመለከተ አጣሪ ቡድኑ ተጫዋቹ ከእነዚህ ተጫዋቾች ጋር በስልክ የተነጋገረው የቀድሞ የክለብ ጓደኞቹ በመሆናቸውና ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለመመካከር እንደሆነም አጣሪ ኮሚቴው አብራርቷል፡፡

ጨዋታው የተከናወነው ሰኔ 17 ሲሆን፣ ከሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም ተጫዋቾች የተለዋወጡትን የስልክ መልዕክት ለማጣራት መሞከራቸውን አቶ ጌታቸው አክለዋል፡፡

ምንም እንኳን በክለቦች አመራሮችና ተጫዋቾች የቀረበው ነገር ምክንያታዊ ቢሆንም፣ በጨዋታው ቀን የሐዋሳ አጥቂና አምበል ጨዋታውን አቋርጠው መውጣታቸው ተገልጿል፡፡

ለሦስት ሳምንት ባከናወነው ማጣራት የደረሰበትን ደረጃ በጋዜጣዊ መግለጫ ያሳወቀው ኮሚቴው፣ ተጫዋቾቹ ጨዋታ ለማጭበርበር መሞከራቸውን እንዳረጋገጠና የሰበሰበውን መረጃ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል፡፡ ቅጣትም የሚያስተላልፈው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መሆኑንም ሳይገልጽ አላለፈም፡፡

ከሁለት ወር በፊት በሐዋሳና ኤሌክትሪክ መካከል የተከናወነው ጨዋታ 1ለ1 የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በደረጃ ሰንጠረዡም ሐዋሳ በ35 ነጥብ 10ኛ ደረጃን በመያዝ፣ ኤሌክትሪክ በ33 ነጥብ የ13 ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ፤ ጅማ አባ ቡና ግን 32 ነጥብ በመሰብሰብ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱ ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...