አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
2 ትልቅ የሰላጣ ሽንኩርት
2 ትልቅ ቲማቲም
2 ኩባያ የተከተፈ ድንች
1 ኩባያ በደቃቁ የተከተፈ ሰለሪ-የሰዴኖ ቅጠል
1 ኩባያ የተከተፈ ካሮት
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
½ የሻይ ማንኪያ በርበሬ
1 የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት ወይም ቅቤ
አዘገጃጀት
- ሽንኩርት ልጦና አጥቦ በስሱና በክቡ መክተፍ፡፡
- ቲማቲሙን አጥቦ በስሱና በክቡ መክተፍ፡፡
- የመጋገሪያውን ዕቃ ካሴሮል ዘይት ወይም ቅቤ መቀባት፡፡
- ድንች፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ሰለሪና ካሮት አንዱን በአንዱ ላይ ጨው እየነሰነሱ በመደራረብ ቅባት የተቀባው ካሴሮል ላይ ማድረግ፡፡
- የተዘጋጀው ካሴሮል ላይ በርበሬና ሚጥሚጣ መነስነስ፡፡
- ዘይት ወይም ቅቤ መጨመር፡፡
- ሙቀቱ 375 ዲግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ለአንስ ሰዓት ወይም እስከሚበስል መጋገር፡፡
ከስድስት እስከ ስምንት ሰው ይመግባል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)