የተገለጡ ዓይኖች
‹‹ከነገሥታት ምግብም ከወይንም የሚጥም፣
ልብን ደስ የሚያሰኝ ስፅፍ አንድ ግጥም፤
ፈጣሪ ከሰጠኝ ከዘመን ፀጋዬ፣
እቀጥላለሁኝ አንድ ቀን በዕድሜዬ፣
ደሞም የማይረባ ዝግንትል፣ ግትልትል፣
ብዕሬ ሲተፋ የቃላት ቅጭልጭል፤
ካነበቡኝ ሰዎች ቅኔ ከጠማቸው፣
እሰርቃቸዋለሁ ያቺን ቀን ከዕድሜያቸው፡፡››
ይህ አንድ አንጓ መሰንበቻውን ለኅትመት በበቃው የሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) የተገለጡ ዓይኖች የግጥም መድበል ላይ የወጣ ነው፡፡ 76 ግጥሞችን ያካተተው ገጣሚው፣ በመጽሐፉ መክፈቻ ላይ ‹‹በጋራ የመገናኛና የመዝናኛ ሥፍራዎች ላይ ሲጋራ ማጨስ የሌሎች ሰዎችን ጤና ይጎዳል›› የሚል ማሳሰቢያ አካትቷለ፡፡ ባለፈው ሳምንት በንባብ ለሕይወት ዐውደ ርዕይ የተመረቀው የመድበሉ ዋጋ 40 ብር ነው፡፡
*****
ዝክረ ተስፋዬ ሳህሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ባለልዩ ተሰጥኦ፣ አንጋፋና ተወዳጁን አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ)ን ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የመታሰቢያ ፕሮግራም ረቡዕ ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዘጋጅቷል፡፡