Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመነሳቱ የእንግሊዙ ኩባንያ የአክሲዮን ዋጋ ከፍ አለ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመነሳቱ የእንግሊዙ ኩባንያ የአክሲዮን ዋጋ ከፍ አለ

ቀን:

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተነሳ በኋላ፣ በኢትዮጵያ የተሰማራው የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያ ከፊ ሚነራልስ የአክሲዮን ዋጋ ጭማሪ ማሳየት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ወርቅ ማዕድን ለማውጣት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰው መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደገው ከፊ ሚነራልስ ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል፡፡

ኩባንያው በምዕራብ ወለጋ በቱሉ ካፒ ያገኘውን የወርቅ ክምችት ለማውጣት ያስችለው ዘንድ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት ጥረት ላይ በነበረበት ወቅት፣ በኦሮሚያና በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንቅስቃሴውን አደናቅፎበታል፡፡ ከፊ ሚነራልስ የወርቅ ማውጫውን ለማስገንባት ከተለያዩ አበዳሪዎችና ከአክሲዮን ሽያጭ ካፒታል በማሰባሰብ ላይ በነበረበት ወቅት ተቃውሞው መነሳቱ፣ አበዳሪዎቹ ለመስጠት ያሰቡትን ብድር እንዲይዙ አስገድዷቸዋል፡፡

ፓርላማው ዓርብ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱ ይታወሳል፡፡ ከፊ ሚነራልስ ይህንን መረጃውን በድረ ገጹ ይፋ ያደረገው አዋጁ ከተነሳ በኋላ ነው፡፡

አዋጁ ከተነሳ በኋላ በነበሩ ቀናት በለንደን ስቶክ ኤክስቼንጅ (የአክሲዮን ገበያ) የከፊ ሚነራልስ ድርሻዎች የዋጋ ጭማሪ ማሳየት መጀመራቸውን ኩባንያው አስታውቋል፡፡ ሰኞ ነሐሴ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በነበረው ገበያ የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ 7.9 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጿል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ ግን በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በባህር ዳር የንግድ ተቋማት ተዘግተው ነበር፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ባለፈው ዓርብ ለፓርላማው ባቀረቡት ሪፖርት፣ በአንዳንድ በውል የሚታወቁ አካባቢዎች የቀሩ አነስተኛ ሥራዎች መኖራቸውንና በመበደኛው የሕግ ማስከበር መቆጣጠር እንደሚቻል መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...