የብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የበልግ አብቃይና አርብቶ አደር አካባቢዎች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በቀጣይ አምስት ወራት ብቻ ከ8.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው የፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልል ሴክተር ቢሮዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎች፣ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ያቸው አገሮችና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያሳተፈው ጥናት ከግንቦት 15 እስከ ሰኔ 15 2009 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡
ቀደም ሲል 7.8 ሚሊየን የነበረው ይህ የተረጂዎች ቁጥር አሁን 8.5 ሚሊየን የደረሰ እንደሆነ ያስታወቀው ኮሚሽኑ፣ ለዚህም የበልግ ዝናብ መዛባት፣ የመኖና ግጦሽ ማነስ ብሎም በአንዳንድ አካባቢዎችም የምርት መቀነስና የውኃ እጥረት ምክንያት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡