Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመረጃ ጠቋሚዎች እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያገኙበት መመርያ ወጣ

መረጃ ጠቋሚዎች እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያገኙበት መመርያ ወጣ

ቀን:

በዳዊት እንደሻው

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለመረጃ ጠቋሚዎች እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት መስጠት የሚያስችል መመርያ አወጣ፡፡

ከሐምሌ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ የሆነው ይህ መመርያ ግብርና ታክስ በሚሰውር፣ በሚያጭበረብር፣ አሳንሶ በሚያስታውቅ፣ ያላግባብ ተመላሽ በሚወስድ፣ እንዲሁም በማንኛውም ሕገወጥ ዘዴ በሚያጭበረብር ግብርና ታክስ ከፋይ ላይ መረጃ እንዲቀርብ ያበረታታል ተብሏል፡፡ ነገር ግን ለተጨባጭ መረጃ ጠቋሚዎች የሚሰጠው ሽልማት አሰጣጥ ተግባራዊ ሲሆን፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ዝርዝር አሠራር ያካተተ ነው፡፡

ይህ መመርያ ከዓመት በፊት ወጥቶ በነበረው ተመሳሳይ መመርያ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡ ለአብነት ያህል የዓምናው መመርያ ለመረጃ ጠቋሚዎች የሚሰጠውን ሽልማት በ10 ሚሊዮን ብር ገድቦ ነበር፡፡ አዲሱ መመርያ ግን ወደ 30 ሚሊዮን ብር አድርሷል፡፡

ከግብርና ከቀረጥ ጋር የተያያዙ ሕገወጥ ተግባራትን በተመለከተ ባለመረጃው በራሱ ጥረት፣ ክትትልና ትንተና ያደረገበት፣ እንዲሁም መረጃው በባለሥልጣኑ ያልተደረሰበትና ሊደርስበት የማይችል ሲሆን ብቻ፣ የቀረበው መረጃ ተቀባይነት ያለው መረጃ ተብሎ እንደሚወሰድ መመርያው ይደነግጋል፡፡

በተቃራኒው በመረጃ አቅራቢው የሚቀርበው መረጃ ምንጩ ከፍርድ ቤት ክርክር ወይም ውሳኔ፣ ከመንግሥት ሪፖርት፣ ከአቤቱታ፣ ከኦዲት ሥራ፣ ከሚዲያና ከመሳሰሉት ሌሎች የኅትመት ምንጮች ሲሆን መረጃው ተቀባይነት እንደማይኖረው ያስታውቃል፡፡

በዚህም መሠረት መረጃ ጠቋሚዎች ባቀረቡት ተጨባጭ መረጃ መሠረት መንግሥት ካገኘው ፍሬ ግብር/ታክስና ወለድ ላይ የሚታሰብ ከአምስት በመቶ እስከ 15 በመቶ የሚሆን የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ፡፡

ለአብነት ዝቅተኛው እርከን ላይ ፍሬ ግብር/ታክስና ወለዱን ጨምሮ እስከ 60 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ መረጃ ጠቋሚው አምስት በመቶ የሚሆነውን ያገኛል፡፡

ሌላው በቀረበው መረጃ መሠረት የተገኘው ፍሬ ግብር/ታከስ እንዲሁም ወለዱ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ከሆነ፣ መረጃ ጠቋሚው 15 በመቶ የሚሆነውን ያገኛል፡፡

መመርያው ለመረጃ ጠቋሚዎች የሚሰጠው ዳረጎት ከ30 ሚሊዮን ብር መብለጥ እንደሌለበት ደንግጓል፡፡ በተለያዩ የእርከን ደረጃዎች የተቀመጡ ለመረጃ ጠቋሚዎች የሚሰጡ የሽልማት ገንዘብ መጠኖች፣ በተለያዩ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ይፀድቃሉ፡፡

በዚህም መሠረት የሽልማቱ መጠን እስከ 10 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ በዋና መሥሪያ ቤቱ የኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ፣ እንዲሁም በቅርንጫፍ ደረጃ የሚደረግ ክፍያ ከሆነ በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ መፅደቅ አለበት፡፡

ነገር ግን የሽልማት መጠኑ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ከሆነ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መፅደቅ አለበት፡፡

ማንኛውም መረጃ ጠቋሚ ያመጣው መረጃ በማታለልና በማጭበርበር ላይ የተመሠረተ ከሆነ፣ ባለሥልጣኑ የሰጠውን ሽልማት ከማስመለስ በተጨማሪ በሕግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚችልም መመርያው ይጠቁማል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...