አስፈላጊ ግብዓቶች
- 2 ኩባያ የፉርኖ ዱቄት፤ የተነፋ
- 1 ኩባያ እርጎ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
- 4 የሾርባ ማንኪያ ማርጋሪን – ቅቤ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
አሠራር
- ዱቄት፣ ጨውና ቤኪንግ ፓውደር አደባልቆ መንፋት፡፡
- ቅቤውን ከተነፋው ዱቄት ጋር በደንብ ቀይጦ እርጎውን ጨምሮ በመጠኑ ማሸት፡፡
- የተቦካውን ሊጥ ትንሽ ዱቄት የተነሰነሰበት ጣውላ ላይ አድርጎ በስሱ መዳመጥ፡፡
- በስሱ የተዳመጠውን ሊጥ በብስኩት ቅርጽ ማውጫ መቁረጥ፡፡
- የተቆረጠውን ሊጥ ቅባት የተቀባ ብስኩት መጋገሪያ ዕቃ ላይ አድረጎ ሙቀቱ 450 ድግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ውስጥ ለአሥራ አምስት ደቂቃ ማብሰል፡፡
ከአሥራ ሁለት እስከ አሥራ አምስት ብስኩት ይወጣዋል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)