Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ታሰሩ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ታሰሩ

ቀን:

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግና የፌዴራል ፖሊስ ዓርብ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤልን በቁጥጥር ሥር አውለዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች ቁጥር ከአቶ ዛይድ ጋር ስምንት ደርሷል፡፡ አቶ ዛይድ የሚጠየቁበት ወይም የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀልና የጥፋት መጠን ባይገለጽም፣ ሌሎቹ ግን ከ646 ሚሊዮን ብር በላይ በሕዝብና መንግሥት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው መሆኑን፣ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አቶ ዛይድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን ለአሥር ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተው፣ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ በትራንስፖርት ሴክተር የቆዩ ሲሆን፣ ሥራ የጀመሩት በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ነው፡፡ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የፕላኒንግ መምርያ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሊድስ ዩኒቨርሲቲ (እንግሊዝ) አግኝተዋል፡፡

በዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ይመራ የነበረው ትራንስፖርት ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ዛይድ፣ ተቀማጭነቱ በካናዳ በሆነው ዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ደኅንነት ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው በቁጥጥር ሥር እስከዋሉበት ቀን ድረስ እየሠሩ ነበር፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...