Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየሙጫ እሳት ራት

የሙጫ እሳት ራት

ቀን:

ትልቁ የሙጫ እሳት ራት እስከ ዛሬ ከሚታወቁት ፍጥረታት ሁሉ በተሻለ፣ በጣም ቀጭን የሆኑ ድምፆችን መስማት ይችላል። ይሁንና የስፒል አናት የሚያክሉት የዚህ ነፍሳት ጆሮዎች የተሠሩበት መንገድ በጣም ቀላል ነው የሚለው ጄደብሊው ዶትኦርግ በሳይንስ ገጹ ነው።

ተመራማሪዎች ይህ የእሳት ራት ያለውን የመስማት ችሎታ ለብዙ ዓመታት ሲያጠኑ ቆይተዋል። ሃቻምና በስኮትላንድ በሚገኘው ስትራትክላይድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ የሳይንስ ምሁራን የተለያየ መጠን ያላቸውን ድምፆች በመጠቀም የዚህን የእሳት ራት የመስማት ችሎታ ለመለካት ሞክረዋል። ‹‹የጆሮ ታምቡሮቹን›› እርግብግቢት ከለኩ በኋላ ለመስማት በሚጠቀሙባቸው የነርቭ ሴሎች ላይ የታየውን እንቅስቃሴ መዘገቡ። የእሳት ራቶቹ እስከ 300 ኪሎ ኸርዝ የሚደርስ ድምፅ መስማት እንደሚችሉ በዚህ መንገድ አወቁ።

በሌላ በኩል የሌሊት ወፎች መስማት የሚችሉት እስከ 212 ኪሎ ኸርዝ የሚደርስ ድምፅ ሲሆን ዶልፊኖች ደግሞ እስከ 160 ኪሎ ኸርዝ የሚደርስ ድምፅ ነው፤ የሰው ልጆች ግን ከ20 ኪሎ ኸርዝ የሚበልጥ ድምፅ መስማት አይችሉም። ተመራማሪዎች የዚህን የእሳት ራት ከፍተኛ የመስማት ችሎታ መሠረት በማድረግ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መሥራት ይፈልጋሉ።

በስትራትክላይድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሠሩት ዶክተር ጄምስ ዊንድሚል የእነዚህን ነፍሳት የመስማት ችሎታ በማየት፣ ‹‹የተሻለ ጥራት ያላቸውና መጠናቸው አነስተኛ የሆነ የድምፅ ማጉያዎችን መሥራት›› እንደሚቻል የተናገሩት፣‹‹እነዚህ የድምፅ ማጉያዎች በሞባይል ስልኮች፣ መስማት የሚቸግራቸውን ሰዎች በሚረዱ መሣሪያዎችና በሌሎች መሣሪያዎች ውስጥ ሊገጠሙ ይችላሉ፤›› በማለት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...