Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከስድስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ይጠቅበት የነበረው የወጪ ንግድ ግማሹን አሳክቷል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

-በመጪው ዓመት ስምንት ቢሊዮን ዶላር ይጠበቃል

በተሸኘው የ2009 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ይጠበቅ የነበረው ገቢ ከ6.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነበር፡፡ ይሁንና ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ብዙም ፈቅ ያላለ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከዘርፉ መገኘቱን ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንም እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሻሻ ቢመጣም የወጪ ንግዱ አፈጻጸም ከሚጠበቀው በታች ሲያሽቆለቁል ቆይቷል፡፡ ለአብነት እንኳ በ2009 በጀት ዓመት ሰባት ወራት ውስጥ የታየው አፈጻጸም ከፍተኛው ቅናሽ የተመዘገገበት እንደነበር የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት አሳይቷል፡፡ በ2009 ዓ.ም. ሰባት ወራት ውስጥ 2.488 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ በአፈፃፀም የተመዘገበው 1.423 ቢሊዮን ዶላር ወይም 57 በመቶ ብቻ  ነበር፡፡

በዚሁ አካሔድ የቀጠለው የአገሪቱ አጠቃላይ የወጪ ንግድ ሁኔታ በዓመቱ ማጠቃለያም ከታቀደው በግማሽ ያነሰ አፈጻጸም በማሳየት አዲሱን በጀት ዓመት ጀምሯል፡፡ ለውጭ ገበያ ከሚቀርቡ ሸቀጦች ውስጥ ምንም እንኳ ቡና የተሻለ አፈጻጸም ቢያሳይም እስከ ሦስተኛው ሩብ ዓመት አጋማሽ ድረስ የነበረው የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ የተንቀራፈፈና ከሚጠበቀው ይልቅ አነስተኛ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁንና እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ በነበረው አካሔድ ግን የቡና የወጪ ንግድ ከሚጠበቀው የ940 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 881 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት ከዕቅዱ የ93 በመቶውን፣ ከሌላውም ጊዜ ይበልጥ ውጤት በማስገኘት ዓመቱን ደምድሟል፡፡

የቅባት እህሎች የኤክስፖርት አፈፃጸም ከዕቅድ አንፃርም ሆነ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት የወቅቱ የሰሊጥ ምርት አቅርቦትና ሽኝት በመቀነሱ ምክንያት ላኪዎች በቂ ምርት አግኝተው በመግዛት የገቡትን ኮንትራት በተገቢው መንገድ ሊወጡ ባለመቻላቸው እንደሆነ ንግድ ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት አመላክቶ ነበር፡፡

ከቁም ከብትና ከሥጋ ለዕቅድ አፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆን እንደምክንያት በዋናነት የምንወስዳቸው በዘርፉ ውስጥ ልምዱ ያላቸው ላኪዎች በብድር አቅርቦት ምክንያት ወደ ገበያ ማቅረብ አለመቻላቸው፣ ሕገ ወጥ ንግዱን መግታት አለመቻሉ  ይጠቀሳል፡፡ የሥጋ ምርትም ከዕቅዱ አኳያ ማሳካት ያልቻለ ሌላው ንዑስ ዘርፍ ሲሆን፣ ዋና ዋና ችግሮች ተብለው ሲጠቀሱለት ከቆዩት ውስጥ በዕቅድ ታሳቢ የተደረጉት ኤክስፖርት ቄራዎችና ላኪዎች በሙሉ አቅማቸው አለመሥራቸው እና የእርድ እንስሳት አቅርቦት እጥረት ዋና ዋና ከሚባሉት ውስጥ ሲጠቀሱ የቆዩ ችግሮች ናቸው፡፡

ለአበባ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ መዳከምም ምክንያቶች አልታጡም፡፡ ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ የአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት ሆኖት ቆጦ ነበር፡፡ በወቅቱ ቅዝቃዜው ከዜሮ በታች ሦስት ዲግሪ ሴልሺየስ ከመውረዱ ምርቱ ቶሎ ማገገም አለመቻሉ እና የተወሰኑ አምራች ድርጅቶች ዝርያ በመቀየር ላይ በመሆናቸው ወደ ማምረት ሒደቱ መግባት አለመቻላቸውም ተዘግቧልል፡፡ ለአትክልትና ፍራፍሬም ተመሳሳዩ የአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት ሆኖ የኤክስፖርት አፈጻጸሙ እንዲቀንስ ሰበብ ሆኖታል፡፡

ለቆዳና ጨርቃጨርቅም እንዲሁ የኩባንያ የውስጥ አስተዳደራዊ ችግሮች፣ የጥሬ ዕጦት፣ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት፣ የገዥዎች ፍላጎት መቀነስ ከሚጠቀሱ ዋና ዋና ችግሮች መካከል ንግድ ሚኒስቴር ሲያቀርባቸው የሰነበቱ የወጪ ንግዱ ችግሮች ናቸው፡፡ ምንም እንኳ የተጠቃለለውን የ2009 በጀት ዓመት ሪፖርት ከንግድ ሚኒስቴር ለማግኘት የተደረገው ጥረት ባይሳካም፣ ከዓምናው የወጪ ንግድ አፈጻጸም ይልቅ ጥቂት ለውጥ እንደታየ ይታመናል፡፡

በዚህ አኳኋን የአገሪቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከሚጠበቀውም ከቀድምት ዓመታትም እየቀነሰ የመጣባቸው ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ተዘርዝረው ቢቀርቡም፣ መንግሥት በዚህ ዓመት ከወጪ ንግድ የሚጠብቀው ገቢ ስምንት ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) በዚህ ሳምንት አስታውቀዋል፡፡ ይህም በአምስቱ ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መሠረት ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻም ከ14 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ የወጪ ንግድ ገቢ እንደሚጠበቅ በሰነዱ ተመልክቷል፡፡

የሸቀጦች ወጪ ንግድ ትንበያ ከ2008 እስከ 2012 (ገቢ በሚሊዮን ዶላር)

ዝርዝር

መነሻ ዓመት

ትንበያ

የ2007 አፈጻጸም

2007

2008

2009

2010

2011

2012

ጠቅላላ የወጪ ንግድ ገቢ

3,019.3

4,884.6

6,780.3

8,747.8

11,035.6

13,909.1

የግብርና ምርቶች ወጪ ንግድ

2,255.9

3,277.4

4,213.0

5,239.2

6,338.4

7,663.9

መደበኛ የግብርና ምርቶች

1,978.9

2,907

3,738

4,556

5,441

6,481

ቡና

780.5

1,022.4

1,339.4

1,607.2

1,870.8

2,173.9

የቅባት እህሎች

510.1

904.5

1,134.2

1,413.3

1,710.0

2,048.6

ጥራጥሬዎች

219.9

318.8

398.5

498.1

622.6

778.3

አትክልትና ፍራፍሬ

47.6

69.0

86.2

107.8

129.4

155.2

የቁም ከብት

148.5

267.3

337.9

425.7

534.7

673.8

ጫት

272.4

324.7

441.6

504.3

572.9

650.8

አበባ

203.1

260.0

339.0

440.3

571.1

742.4

ሌሎች የግብርና ምርቶች

73.9

110.7

136.2

242.4

326.8

440.8

የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ

419.9

992.7

1,852.6

2,332.2

3,118.6

4,199.2

ማኑፋክቸሪንግ

377.1

864.6

1,313.6

1,801.3

2,534.5

3,556.8

ቆዳና የቆዳ ውጤቶች

131.6

206.6

272.7

368.1

505.0

706.5

ስጋና የስጋ ውጤቶች

92.8

112.3

146.0

192.7

263.4

374.1

የጨርቃጨርቅ ውጤቶች

98.9

184.0

270.5

397.9

556.7

778.8

ስኳርና ሞላሰስ

0.0

138.0

265.0

327.0

435.8

586.2

ምግብና መጠጥ

21.5

25.7

44.3

88.6

154.3

268.0

ኬሚካል

18.9

27.5

49.8

62.9

81.1

101.3

ፋርማሲቲካልስ

2.7

29.6

54.8

69.0

89.2

111.4

የብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ውጤቶች

10.5

92.1

121.1

181.5

302.9

448.0

የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች

0.2

48.9

89.4

113.6

146.0

182.4

ኤሌክትሪክ ሀይል

42.8

128.0

539.0

530.9

584.0

642.4

የማዕድን ወጪ ንግድ

345.73

500.35

780.75

1,049.91

1,470.39

2,011.01

ምንጭ፡- ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን፣ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የተጠቃለለ ሰነድ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች