Saturday, June 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቢሲኒያ ባንክ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በማበደር ዓመቱን አገባደደ የተበላሸ የብድር

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

አቢሲኒያ ባንክ የ2009 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሰጠው የብድር መጠን በ73.3 በመቶ በማሳደግ 14.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ደግሞ ከ 20.7 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተገለጸ፡፡

ባንኩ የ2009 ዓ.ም. በጀት ዓመት አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለሪፖርተር በላከው መረጃ በቀዳሚው ዓመት መጨረሻ ላይ 8.14 ደርሶበት የነበረውን የብድር መጠን በአራተኛ ደረጃ በማሳደግ በባንኩ ታሪክ ከፍኛ ሊባል የሚችለውን ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ግን የብድር መጠኑን በከፍተኛ ደረጃ ከማሳየቱም በላይ ባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ለማሳደግ ባካሄደው እንቅስቃሴ በቀዳሚው ዓመት መጨረሻ ላይ አሰባስቦት ከነበረው ተቀማጭ ገንዘብ 52 በመቶ በመጨመር በ2009 ዓ.ም በጀት ዓመት 20.7 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ አምና በተመሳሳይ ወቅት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 13.6 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

ለተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ዕድገት አስተዋጽኦ ካበረከቱት ዕርምጃዎች አንዱ በበጀት አውታሩ 27 አዳዲስ ቅርንጫፎች መክፈቱ ነው፡፡ አዳዲሶቹ ቅርንጫፎች መክፈት በበጀት አውታሩ መጨረሻ ላይ ባንኩ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ቁጥር በ26 በመቶ በማሳደግ 233 አድርሶለታል፡፡  

እንደባንኩ መረጃ ለተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ዕድገት የባንኩን አስቀማጭ ደንበኞች ቁጥር ከቀዳሚው ዓመት በ28 በመቶ ማደግ በመቻሉ ነው፡፡ እንደ መረጃው በ2009 መጨረሻ ላይ 585,735 የነበረው ደንበኞች በተጠናቀቀው በጀት 750 ሺሕ መድረሱ ለአብነት ተጠቅሷል፡፡

ባንኩ በዚህን ያህል ደረጃ የብድር መጠኑ ቢያድግም በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው የተበላሸ ብድር መጠን () 1.41 በመቶ ብቻ ነው፡፡

በቀደመው ዓመት ደግሞ ዝቅተኛ የተበላሸ ብድር መጠን ካላቸው ባንኮች ውስጥ አንዱ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን በወቅቱ የተበላ ብድር መጠኑ 1.9 በመቶ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ግን ይህንንም ወደ 1.4 በመቶ መውረዱ እንዲሁም ዝቅተኛ የተበላሸ ብድር መጠን ካላቸው ባንኮች ተርታ ተሠልፏል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ድንጋጌ ባንኮች የተበላሸ ብድር መጠየቃቸው ከ5 በመቶ መብጥ የለበትም፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘው ወቅታዊ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ የ2009 በጀት ዓመት የባንኮች አማካይ የተበላሸ የብድር መጠን 3 በመቶ ነው፡፡

የ2009 በጀት ዓመት የትርፍ መጠኑን በተመለከተ የተለካው መረጃ ደግሞ ባንኩ ከታክስና ፕሮቬዥን ማይቀነስ 801 ሚሊዮን ብር አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ ፕሮቪዥን ሲቀነስ ከታክስ በፊት ከ730 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ሊያመዘግብ እንደሚችል ይገመታል፡፡

አቢሲኒያ ባንክ በበጀት ዓመቱ መጀመርያ ላይ የባንኩን ካፒታል ወደ 4 ቢሊዮን ብር ለማድረስ የወጠነ ሲሆን በዘርፉ መሠረት የተከፈለ ካፒታሉን እየሠራ ነው፡፡ ይህንን ውሳኔ ዓመት ባለፈበት ወቅት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 1.27 ቢሊዮን ብር ሲሆን ለ2009 ዓ.ምም መጨረሻ ላይ ደግሞ በ41 በመቶ በማድረግ 1.8 ቢሊዮን ብር ለማድረስ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ወቅት 5,005 ሠራተኞች ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ይህም 20.8 በመቶ ሚሊዮን ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች