Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹አዲስ አባባ›› ወይስ ‹‹አዲስ አበባ››

ትኩስ ፅሁፎች

የዛሬን አያርገውና የአዲስ አበባ ስም ከ76 ዓመታት በፊት በእንግሊዝኛ ፊደላት ሲፃፍ የነበረው ልከኛው አፃፃፍ! ‹‹ADDIS ABEBA›› ነበር፡፡ በዘመናችን ‹‹አዲስ አበባ›› በእንግሊዝኛው ዘር ሲፃፍ ግን አላግባብ ‹‹ADDIS ABABA›› አዲስ አባባ እየተባለ  ነው። ፎቶው ኢትዮጵያን ከፋሺስት ጣሊያን ቀንበር ለማላቀቅ ከአርበኞች ጎን ተሰልፎ በደቡብ ግንባር መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገባው የእንግሊዝ ጦር ከአዲስ አበባ ሰሌዳ ጋር ይታያል።

አንዲቱን ቀዘባ

እንደ ሐምሌ ወራት ፊቷ ጭፍና ለብሶ፣

እንደ መኸር ድርቆሽ ልብሷ ተልከስክሶ፣

አየኋት ለየኋት አንዲቱን ቀዘባ፣

ዘንጠፍ ዘና ብላ እንደ መስክ አበባ፡፡

ፊቷ ጭፍና ቢለብስ፣

ልቧሷ ቢልከሰከስ፣

ግና ሥግው ሆኖ ውበት ተደብቆ፣

ታየኝ ተገለጠ ድንገት አሸብርቆ፡፡

ልብሷ የባላገር፣ አየሯ ገጠር፣

ኩለንታዊ ውበት ይዛ የምትኖር፣

አየኋት ከመስኩ ወደ ገጠር ሄጄ፣

ተፈጥሮን ስፈልግ ተፈጥሮን ወድጄ፡፡

ነባይ አባል ማለት በተፈጥሮ ቤት

አንዲቱ ቀዘባ አክሊል የውበት፣

ያልተዳደፈችው በሰው ሠራሽ ፈሊጥ ከንቱ ፈንደላላ፣

አየኋት አየኋት የገጠሯን ስንድቅ የገጠሯን አፍላ፡፡

  • ዮሐንስ አድማሱ (ነሐሴ 1954 ዓ.ም.)

***

 

በድምፅ የሚታዘዝ ፈርኒቸር ተሠራ

በድምፅ፣ በሞባይል አፕሊኬሽን የሚታዘዝ ፈርኒቸር ተሠራ፡፡ በጠባብ ክፍል ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እፎይታ የሚሰጠው ፈርኒቸር ቁምሳጥን፣ አልጋና ሶፋዎችን ያካተተ ነው፡፡ ከሉበት ቦታ ሳይነሱ ቤትዎን እንደፈለጉ ማስተካከል ቦታ መቀያየር የሚያስችል ነው፡፡ ቁም ሳጥኑም አንድን ክፍል ለሁለት መክፈል የሚችል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ፈጠራው በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ዲዛይን የተደረገ ነው፡፡ በከፍተኛ መጠን ሊያመርቱለት የሚችሉ አካላትን የማሳመን ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡

***

የኮኮናት ዛፍ በመውጣት ከዓለም አንደኛ የሆነው ወጣት

          የኰክ አይስላንደሩ ጆርጅ ሎና የኮኮናት ዛፍ በመውጣት ሪከርድ ጨብጦ በዓለም ግንባር ቀደምትነትን ተቆናጧል፡፡ የኮኮናት ዛፍ በመውጣት ስፖርት ዘርፍ አንደኛ የወጣው ወጣት ስምንት ሜትር የሚሆነውን ዛፍ በ5.62 ሰከንድ አጠናቋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በታሒቲ ሙዚየም በተካሄደው ውድድር ተወዳዳሪዎች ዛፉን የሚወጡበትን ሰዓት ለማሻሻል ሁለት ዕድል የተሰጣቸው ሲሆን፣ ጆርጅ ሁለተኛ ከወጣው አሜሪካዊው ሳይሶ ፊፖይ በእጥፍ በልጦ ተገኝቷል፡፡ ተወዳዳሪዎች በቁርጭምጭሚታቸው ዙሪያ በተደረገ ገመድ እየታገዙ ሲወዳደሩ በአንክሮ ይከታተሉ የነበሩ ታዳሚዎች አሜሪካዊው ውድድሩን በድል ያጠናቅቃል ብለው ቢገምቱም፣ ጆርጅ በድንገት ዛፉ ጫፍ ደርሶ አንደኝነቱን አረጋግጧል፡፡ ‹‹በማሸነፌ ተደስቻለሁ፤ ኮርቻለሁም፤›› ብሏል ውድድሩን ሲያጠናቅቅ፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች