Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፈው አሥረኛው ማስተር ፕላን ፀደቀ

በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፈው አሥረኛው ማስተር ፕላን ፀደቀ

ቀን:

  • የግንባታ ቁጥጥር ባለሥልጣን በድጋሚ ተቋቋመ

በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፈው አሥረኛው የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ሐሙስ ሐምሌ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ፀደቀ፡፡

ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 2006 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አሥር ዓመታት የተተገበረው ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን፣ የመጠቀሚያ ጊዜው ከሦስት ዓመታት በፊት ተጠናቋል፡፡

ነገር ግን አሥረኛው ማስተር ፕላን በወቅቱ መድረስ ባለመቻሉ፣ አዲስ አበባ ላለፉት ሦስት ዓመታት ይፋ ማስተር ፕላን ሳይኖራት ቆይቷል፡፡

በዋናነት ይህ ሊሆን የቻለው አዲስ አበባ ከተማ ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር የተጣጣመ የጋራ ፕላን ሊኖር ይገባል በመባሉና ይህንን ሥራም ለሁለቱ አስተዳደር አካላት በጋራ እንዲዘጋጅ በመወሰኑ ነው፡፡

የሁለቱ አስተዳደር አካላት የጋራ ማስተር ፕላን ከተዘጋጀና ለውይይትም በቀረበበት ወቅት ተቃውሞ በመነሳቱ፣ ተቃውሞውም ደም አፋሳሽ ስለነበረ በኦሮሚያ በኩል ያለው የማስተር ፕላን ዝግጅት እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡

በመጨረሻ ከአምስት ዓመታት ዝግጅት በኋላ ለአዲስ አበባ ብቻ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን ለምክር ቤት ቀርቦ ሊፀድቅ ችሏል፡፡

አዲሱ ማስተር ፕላን አምስት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም የመሬት አጠቃቀም፣ የመንገድና የመጓጓዣ መረብ፣ የሕንፃ ከፍታ፣ የፕላን መጠቀሚያ ሰነድ፣ የከተማ ፕላን የአሠራር ደንቦች፣ ሙያዊ ልምዶችና የደረጃ መመርያዎች ናቸው፡፡

የመሬት አጠቃቀም ፕላኑ 14 ዓበይት ጉዳዮች ያካትታል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ቅይጥ የንግድ ሥራና የገበያ ሥፍራ፣ አስተዳደራዊ አገልግሎት፣ ማኀበራዊ፣ ማዘጋጃ ቤታዊ፣ የመጓጓዣ ማዕከላት፣ የከተማ ግብርና፣ ማምረቻና ማከማቻ፣ ታሪካዊ ሕንፃዎችና ጥብቅ ቦታዎች ይገኙበታል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ማስተር ፕላኑ በፀደቀበት ወቅት እንዳሉት፣ በማስተር ፕላኑ መሠረት አዲስ አበባ የምታድገው ወደ ጎን ሳይሆን ወደ ላይ ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረትም የሕንፃ ከፍታና ጥግግት ጉልህ ሥፍራ ይኖረዋል፡፡

ይህ ማስተር ፕላን ከሌሎች ዘጠኝ ማስተር ፕላኖች የሚለየው፣ በትክክል መተግበሩን የሚከታተልና የሚቆጣጠር ተቋም በመቋቋሙ ነው፡፡

በየካቲት 2009 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን ኮሚሽን ተቋቁሟል፡፡

ይህንን ተቋም በማስተር ፕላኑ ዝግጅት ወቅት ጉልህ ሥፍራ የነበራቸውና የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩት አቶ ማቲዮስ አስፋው ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተለያዩ ኃላፊነቶች ተጨምረውለት፣ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሠረተ ልማት ቅንጅትና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን›› ተብሎ ሐምሌ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. በድጋሚ ተቋቁሟል፡፡

ባለሥልጣኑ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደር አካላትን ጨምሮ ማንኛውም የመሠረተ ልማት ገንቢ በሚፀድቅለት ፕላንና ዲዛይን መሠረት እንዲገነባ ማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና የተቀናጀ የግንባታ ልማት አተገባበር ሥርዓት እንዲከተል የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...

ማን ይቻለን?

በጠዋት የተሳፈርንበት ታክሲ ውስጥ በተከፈተው ሬዲዮ፣ ‹‹ይኼኛው ተራራ ያን...