Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከበጀት ዓመቱ ጋር የሚጣረሰው የፌዴሬሽኖች ጉባኤና ምርጫ

ከበጀት ዓመቱ ጋር የሚጣረሰው የፌዴሬሽኖች ጉባኤና ምርጫ

ቀን:

ከአዲሱ ሩብ በጀት ዓመት በኋላ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ፣ ላለፉት አራት ዓመታት የቆየውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራር ለማሰናበት ወይም እንዲቀጥል የሚያደርገውን አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫም እንደሚያካሂድ ይጠበቃል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚያካሂደው ጉባኤና ምርጫም እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ከመስከረም በኋላ ባሉት ወራት ካልሆነ ከዚያ ወዲህ እንደማይካሄድ ከፌዴሬሽኑ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

እንደ መረጃው ከሆነ የፌዴሬሽኑ መደበኛው ጉባኤ በየዓመቱ ወቅቱን ጠብቆ ተካሂዶ ያውቃል ለማለት ያስቸግራል፡፡ ነባሩ አመራር ከቀድሞቹ ሲረከብ በዘገየ አካሄድ የበጀቱን ዓመት ጠብቆ ባለመሆኑ ተረካቢውም ጉባኤውንም ሆነ በየአራት ዓመቱ የሚያካሂደውን የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ወቅት እያዛባ ለመጓዝ እንደተገደደ ያመለክታል፡፡ ይህም ሆኖ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የዘንድሮውን ጉባኤም ሆነ ምርጫ ከመስከረም 2010 ዓ.ም. በኋላ ለማካሄድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኦዲት ሪፖርቱንም ሆነ የክንውን ሪፖርቱን በማዘጋጀት ላይ በመሆኑ ጉባኤውን ወደ ሩብ ዓመቱ መጨረሻ መግፋቱን የፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በተለይ ለሪፖርተር ይገልጻሉ፡፡

እንደ አቶ ወንድምኩን፣ ፌዴሬሽኑ በተለይም በአሁኑ ወቅት የኦዲትና የክንውን ሪፖርቶችን እያዘጋጀ እንደሚገኝና እንደተጠናቀቀም ጉባኤው በምን አግባብ እንደሚካሄድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በጉዳዩ ተወያይቶበት ውሳኔውን ይፋ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

የዘንድሮው ጉባኤ ከኦዲትና ከክንውን ሪፖርት ዝግጅት በተጨማሪ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ለቀጣዩ አራት ዓመት ተቋሙን የሚያስተዳድሩ አዳዲስ የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫም የሚካሄድ በመሆኑ፣ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደግሞ ተወካዮቻቸውን ምርጫው ከሚከናወንበት 45 ቀን በፊት ለፌዴሬሽኑ ማሳወቅ ስለሚጠበቅባቸው ለዚህ ደግሞ ጊዜ የሚያስፈልጋቸው እንደሆነ ጭምር ይገልጻሉ፡፡

ይህንን የፌዴሬሽኑን ምክንያት የማይቀበሉ ወገኖች አሉ፡፡ ከነዚህ ወገኖች መካከል የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ይጠቀሳሉ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ሚያዝያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ ብዙዎቹ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ጉባኤዎቻቸውንም ሆነ ምርጫ የሚያከናውኑት የአገሪቱን የበጀት ዓመት መነሻ ያደረገ እንዳልሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹እውነቱን ለመነጋገር የሚኒስቴሩ ድጋፍና ክትትል የሚመራው የአገሪቱን የበጀት ዓመት መነሻ አድርጎ ነው፡፡ ምናልባት በተለየ ሁኔታ እንዲታይ አስገዳጅ የሚሆነው የኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ነው፡፡ ምክንያቱም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ጉባኤንም ሆነ ምርጫውን እንዲያደርግ የሚገደደው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ሁሉም ጉባኤያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው፡፡ እየሆነ ያለውም ይኼው ነው፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ግን የአገሪቱን የበጀት ዓመት እንዲያከብሩ ይገደዳሉ፡፡ ስለዚህ አሁንም በዚህ ረገድ በሁሉም ፌዴሬሽኖች ውስንነት እንዳለ እንረዳለን፡፡ እስከነአካቴው ጉባዔም የማያደርጉ አሉ፡፡

የሚኒስቴሩ ድርሻ የሚሆነው የዕውቅና አሰጣጥ ጉዳይ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሰመሩበት፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በደንብና መመሪያዎቻቸው መሠረት ማድረግ ያለባቸው የአገሪቱን የበጀት ዓመት መነሻ ያደረገ አሠራር ሊከተሉ እንደሚገባ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉም ተገቢው ዕውቅና እንደሚሰጥ፣ በ2003 ዓ.ም. በወጣው የማኅበራት አደረጃጀትን የሚመለከተው መመሪያ መሠረት፣ ፌዴሬሽኖች አሠራራቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንደሚጠበቅባቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ተቋማቱ የሕዝብ እንደመሆናቸው ለፓርላማ ቀርበው አፈጻጸማቸውን እንዲያስረዱ የተደረገበት አግባብ አለ›› በማለት የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ጉባኤና ምርጫ ከበጀት ዓመቱ ጋር ምን ያህል የተጣረሰ መሆኑን ማብራራታቸው አይዘነጋም፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...