‹‹ውሳኔ መስጠት የሚያስችለን ወቅታዊ የሆነ መረጃ አለን ወይ? እኔ እርግጠኛ ነኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውስጥ መረጃ አለኝ ብዬ ለመናገር የሚያስችል አፍ የለኝም!!››
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት (The Road to Deliverology 101) የተሰኘ የአሠራር ጽንሰ ሐሳብ ትግበራ አስመልከቶ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተዘጋጀ መድረክ ላይ የተናገሩት፡፡ በኢቢሲ ሐምሌ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲተላለፍ እንደታየው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹በየመሥሪያ ቤታችን ኳሊቲ መረጃ አለን ወይ?›› ብለው ጠይቀው፣ ውሳኔ የሚሰጡትም ‹‹ሰዎች በተናገሩት ላይ ተመሥርቼ ነው እየወሰንኩ ያለሁት፤ በጣም ወቅታዊ የሆነ ታች ያለች መረጃ አግኝቼ በዚያ መረጃ ላይ ተመሥርቼ ውሳኔ እየሰጠሁ ነው ብዬ ነው ለማለት አልችልም፡፡ አያንዳንዳችሁ እንደዚያ እንደሆናችሁ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ፤›› ብለዋል፡፡