Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ጊዜ ወርቅ ነው ሥሩበት አይሥራባችሁ››

ትኩስ ፅሁፎች

ይህ ሐውልት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ለ፲፪ (12) ተማሪዎች መመሪያ ሲሰጡ የሚያሳይ ሲሆን ቀደም ብሎ ሐውልቱ በሀገር ፍቅር ቴአትር ለረዥም ጊዜ ቆሞ የነበረ ሲሆን በ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም. የዘውድ አገዛዝ ሲያበቃ በጊዜያዊ ወታደራዊ
አስተዳደር ደርግ መንግሥት ከቦታው እንዲነሣ ተደረገ:: በኋላም በ፲፱፻፷፰ (1968) ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የገባ ሲሆን ከዚያም በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጥገና ተደርጎለት ሰኔ ፳፻፬ (2004) ዓ.ም. ለሕዝብ እይታ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል::

***

 

አገር ሙሽራ ነች
ከመንገድ ተጠልፋ…በጠላት ብትወድቅም..
ጀርባዋን ተገርፋ…ሰንበር ብታተርፍም…
በመከራ ታማ…የማትድን ብትመስልም…
አገር ሙሽራ ነች…ውበቷ የሚጎላ
እንደቀድሞው አምራ…ደስታን የምትሞላ
ሰንሰለት በጥሳ…ድል አርጋ የምትመጣ
ታዳሚን አክባሪ…ደምቃ የምትወጣ::
በረሃብ በድካም…በስቃይ ብታልፍም
ሃዘኗ አይሎ….እንባ ብታፈሰም
ብርታት ማሸነፍን …በልቧ የከተበች
ተስፋ የማትቆርጥ….አገር ሙሽራ ነች::

ከትልቁ ድንኳን …ብርሃን ከሞላው
ሃር ከለበሰው ….የሚለይ ከሌላው 
ከድግሱ ስፍራ …ሲደርስ ሰርገኛው 
እንደ እንቁ አምራ …የምታልፍ ታጅባ 
አገር ሙሽራ ነች….በድል የምትገባ::

  • ሳምሶን ጌትነት

 

***

በዶናልድ ትራምፕ መልክ የተሠራ የፊት መሸፈኛ በማድረግ

ባንክ የዘረፉ

ጉዳዩ የተፈጸመው በጣሊያን ነው፡፡ በሰሜናዊ ጣሊያን በምትገኘው ቱሪን ከተማ የ26 እና የ30 ዓመቶቹ ወንድማማቾች ከባንክ የኤቲኤም ማሽን ለመዝረፍ ያቀዱት፣ ፊታቸውን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምሥል የተቀረፀ የፊት መሸፈኛ (ማስክ) በመጠቀም ነበር፡፡

ሮይተርስ እንዳሰፈረው፣ ወንድማማቾቹ ፊታቸውን በማስኩ ከመሸፈናቸው ባለፈም፣ ነጩን ማርሴዲስ መኪናቸውን፣ ጥቁር ቀብተውት ነበር፡፡ ወንድማማቾቹ ከብዙ የኤቲኤም ማሽኖች ውስጥ ገንዘብ በመዝረፍ ተጠርጥረው በጣሊያን ፖሊስ የታሰሩ ሲሆን፣ ሲያዙም ትራምፕ መሳዩን ማስክ እንዳጠለቁ ነበር፡፡

***

ቲማቲምን መሣሪያ በታጠቁ ጠባቂዎች

በህንድ የቲማቲም ዋጋ መናርን ተከትሎ የሚደረግ ዝርፊያን ለመከላከል የታጠቁ የመከላከያ አባላት ተመደቡ፡፡ ቢቢሲ እንደሚለው፣ በህንድ ኢንዶሬ ከተማ አንደ ሮኬት የተተኮሰውን የቲማቲም ዋጋ ተከትሎ፣ ቲማቲም በትላልቅ መኪኖች ተጭኖ በሚጓጓዝበትም ሆነ፣ ገበያ ከገባ በኋላ በታጠቁ ወታደሮች እንዲጠበቅ የተደረገው፣ በአገሪቱ የቲማቲም ዋጋ ማሻቀብን ተከትሎ ዘራፊዎች በሺዎች ሩፒ (የህንድ ገንዘብ) ዋጋ የሚያወጣ ቲማቲም ከየስፍራው በመዝረፋቸው ነው፡፡ በህንድ በሁሉም የምግብ ዓይነቶች የሚጨመረውና ዋና ምግብ የሆነው ቲማቲም፣  በኪሎ 100 ሩፒ ወይም 1.55 ዶላር እየተሸጠ መሆኑንም ዘገባው ያሳያል፡፡

***

ተንቀሳቃሽ ሻወር በጀርባው አዝሎ የሚዞር ቻይናዊ

በቻይና ሰሞኑን የተከሰተውን ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ አንድ ወጣት መንገደኞችን ማስገረሙን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡ ወጣቱ በጀርባው ባዘለው ቦርሳ ውስጥ ከኬሚካል መርጫ መሣሪያ በተሠራ ዕቃ ውኃ ሞልቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ባቡር በሚጠብቅበትና ሙቀቱ በሚያይልበት ጊዜም፣ ከጀርባው ካዘለው ሻወር ውኃ በመጠቀም ራሱን ያቀዘቅዛል፡፡ ይኼም የመንገደኞችን ቀልብ ስቧል ሲል ዩፒአይ አስፍሯል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች