Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ንብ

ቀን:

ንብ ባለክንፍ ተንቀሳቃሽ፣ ተባትን እንስት አበባን ኹሉ እየቀሰመች የምትጋግር፣ የማር ዐበዛ፣ ትጉ (ትግህት) ሠራተኛ፡፡ ቀፎዋን የነካባትን እሾኽ በሚመስል ፍላጻዋ ጦር መሣሪያዋ (መርዟ) ትነድፋለች፡፡ ዐርኬና በሚባል ዕልፍኝ የሚውሉ ባጀብ የሚኼዱ አውራ ንጉሥና ንግሥት ውኃ ቀጂ ድንጉል አሏት፡፡ አውራው ከንግሥቲቱ ጋር ተራክቦ ካደረገ በኋላ ንቦቹ ይገድሉታል ይባላል፡፡ ከንግሥትም ንግሥት በተወለደች ጊዜ የናቷን ሠራዊት ከፍላ ከቀፎ ወጥታ ታጅባ ወደ ሌላ ሥፍራ ትኼዳለች፡፡ ሥነ ሥርዐቷ አይቃወስም፡፡

ሙያን ኹሉ የምታውቅ ሴት በምሳሌ ንቡት  ትባላለች፡፡

ካፏ ማር ይዘንባል ከከንፈሯ ጠጅ

ወይዘሮ ንቡት የትጋት ወዳጅ፡፡

‹‹ንቦ ንቦ አትናደፊ፣

የነከሌ ነኝ ብለሽ እለፊ፤›› እየተባለም ይዜማል፡፡

  • ደስታ ተክለወልድ ‹‹ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› (1962)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...