Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

  የሳምንቱ ገጠመኝ

  ቀን:

  የተማረ ብዙ አወቀ፣
  ብዙ ያወቀ ጠማማ መንገድን ናቀ፣
  ጠማማ መንገድን የናቀ በድህነት ማቀቀ፣
  …..ከዚያም ዓይኑ እያየ ወደቀ፣
  የመዥገር መረማመጃ ሆነና
  ታሪኩ በቃ አለቀ።

  ያልተማረ አላዋቂ …..፣
  ድሮ ድሮ ተናቀ፣
  ዛሬ ዛሬ፣
  ….‹‹የተናቀ አስረገዘ››፣
  ተባለና ተደነቀ።

  በፎርጂድ ዲግሪው ተደነቀ፣
  በሀብትና ሥልጣን ተጥለቀለቀ፣
  በምሁራን ‘ሊስት’ ውስጥ ታጨቀ፣
  አለቀ።

  ፐ!!!!!!!!!….. (((ቅኔ ብሎ ዝም!!))

  ሰሞኑን የተጀመረው የትምህርት ማሰረጃ ማጣራት ጉዳይ ጉድ እያፈላ ነው። ፖሊስ፣ ‹‹ይህ የእናንተ ተማሪ ነበር?›› እያለ በስማቸው የታተመ ዲግሪና ማስተርስ እንዲያጣሩ የሚያቀርብላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከእነሱ ባልወጣ ማስረጃ ከመምህር እስከ ኢንጂነር… ከአስተዳደር እስከ ሐኪም… ስንቱ የሥራውን ዓለም ሲያንቦጫርቀው መኖሩ እየደነቃቸው ‹‹አጀብ!›› እያሉ ነው። አንዳንድ ወዳጆቻችንም ፌስቡክ ላይ ይህንኑ እያወሩት ነው።

  ለዓመታት በጥናት አንገት ደፍተው የኖሩ ስንት ትንታጎች የሥራ ማስታወቂያ ባለበት እንደ ዝንብ ሲራኮቱ በምንታዘብበት ዓይናችን ስንቱ ‹‹ድልብ ማይም›› ፎርጂድ ወረቀት ይዞ በአቋራጭ ሲዘንጥብን መኖሩን ማየት ማናደድ ብቻ ሳይሆን ያስቀውሳል!!… ዲግሪና ማስተርስ ተገዝቶለት ሥልጣን የተሰጠው መዥገር ደግሞ፣ አሁንም ሕዝብ ላይ ተጣብቆ ደም እየመጠጠ መኖሩ መቼ እንደሚያበቃ ማወቅ እንሻለን።

  ለማናቸውም የቀደመውን ጽሑፌን በዚህ አጋጣሚ ‹‹ቢስ›› ብየዋለሁ!! የዚህች አገር ዜጋ ከሆንክ ሕይወትን እንዲህ የግልብጦሽ ትኖራታለህ። ከሚያውቅ ሰው ይልቅ ያወራ ከብሯል። የሐሰት ወረቀት የያዘ የዕውቀት ኮሮጆ ከሆነው ሰው በልጦ ቁልፍ፣ ቁልፍ ቦታ ይዟል። በዕውቀት ተመርኩዞ መናገር አስጠርጥሮ አላዋቂ መስሎ መኖር አስከብሯል። ፍሬው ከብዶት ካጎነበሰው ዛፍ የበለጠ ባዶ ቅጠል ተሸክሞ የቆመ ‘መፋቂያ’ ለሹመትና ሽልማት ተመርጧል። አዋቂ ሰው ባላዋቂ መንገድ መጓዝ የተሻለ እንደሆነ አስቦ አፉን ለጉሟል።

  አዕምሮውን በዕውቀት ያመቀ ዝም ሲል ባዶ ጭንቅላትና ሰፊ አፍ የያዘው ከምሁር ተርታ ተጥፏል። ስታትስቲክሱ ላይ ዲግሪና ማስተርስ ተጽፎለታልና ያልለፋበትን ቁጭ ብሎ ይበላል። ይቺ አገር ከጭንቅላት ይልቅ ለአፍ ቅድሚያ ሰጥታለችና ገና ወዮላት። በየቤቱ ባለሰፊ አፍ የመፋቂያ ዛፎች ፍሬ የተሸከመውን ቅርንጫፍ እየቆረጡ ሲጥሉት ስናይ ፈራን!!… ይቺን አገር ቦርቡረው ባዶ ስልቻ እያደረጓት መሆኑን ስናስብም ፈራን!!….ፈራን…..ፈራን….ባዶ ጭንቅላት ፈራን፡፡

  (መላኩ ብርሃኑ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...