Sunday, April 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየእንቁራሪት መሰል ዝርያው ሳላማንደር

የእንቁራሪት መሰል ዝርያው ሳላማንደር

ቀን:

ሳላማንደር የእንቁራሪት አስተኔ ዝርያዎች ውስጥ ከሚካተቱት አንዱ ነው፡፡ ሳላማንደሮች ከእንቁራሪት ጋር ሲተያዩ በጭራቸው፣ ከሴሲሊያን ጋር ሲነፃፀሩ በእግራቸው የሚለያዩ ናቸው፡፡ ረዥምና ሸንቃጣ አካል ሲኖራቸው አካላቸው ላይ ምንም ቅርፍ አይገኝም፡፡ እግርና ጅራትም አላቸው፡፡ እግራቸውም እንደ እንሽላሊት ዓይነትና በደንብ ያልዳበረ ነው፡፡ በአመጋገባቸው ሥጋ በል ናቸው፡፡

ርባታቸው እንደ ሴሲሊያን ውስጣዊ ፅንሰት በማካሄድ ነው፡፡ የዕጭ ዕድገት ደረጃቸው በውኃ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ የጉልምስ ዕድገት ደረጃቸው ደግሞ የብስ ላይ ይታያል፡፡ የተለያዩ ዓይነት የመተንፈሻ ክፍለ አካል በተለያየ የዕድገት ደረጃቸው ላይ ያሳያሉ፡፡ በዕጭ የዕድገት ደረጃ በስንጥብ፣ በጉልምስ የዕድገት ደረጃ ደግሞ በሳንባ የሚተነፍሱ ይሆናሉ፡፡

ብዙዎቹ ቅርፀተ ለውጥ የሚያካሂዱ ሲሆን፣ በዕጭነት ጊዜያቸው በስንጥብ እየተነፈሱ በውኃ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ በጉልምስ (ሙሉ አካል በሚይዙበት) ጊዜ ደግሞ በሳንባ እየተነፈሱ ረጠብ ያለ ፅንሰት ያካሂዳሉ፡፡ ይህም ማለት የወንዱ ነባዘርና የሴቷ እንቁላል የሚገናኙት ሴቷ አካል ውስጥ ነው ማለት ነወ፡፡ በአንፃሩ በእንቁራሪቶች ይህ የሚሆነው ውኃ ውስጥ ነው፡፡ ይህም ውጫዊ ፅንሰት ይባላል፡፡

ሳላማንደርን አንድ በጣም ለየት የሚያደርጋቸው ነገር አላቸው፡፡ ይኼውም አክዞሎትል የሚባለው ዝርያቸው ነው፡፡ ይህ ዝርያ በእጭ የዕድገት ደረጃ እያለ (ጉልምስነት ላይ ሳይደርሱ) መራባት የሚችል ነው፡፡ ይህም በአብዛኛው እንስሳት የሚታይ ባለመሆኑ አስደናቂ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

  • ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኦቲዝምን ለመቋቋም በጥምረት የቆሙት ማዕከላት

ከኦቲዝም ጋር የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ...

አወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ

የአማራና ትግራይ ክልሎችን እያወዛገበ ያለው የወልቃይት ጉዳይ ዳግም እየተነሳ...

ተጠባቂው የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር መለኪያ የሆነው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር የሞባይል ስልክን በመጠቀም ሊገኙ የሚችሉ የፋይናንስ...

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት...