አስፈላጊ ግብዓቶች
- ግማሽ ኪሎ ዓሣ፣ ለጥብስ የሚሆን
- 1 ወይን፣ 2 ቀይ ሽንኩርት
- 1 ሎሚ
የተፈጨ ዳቦ
ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ
ዘይት፣ ለመጥበሻ
- ዓሣውን በደንብ አጥቦ በተፈጨ ዳቦ፣ በጨውና በቁንዶ በርበሬ ውስጥ እየነከሩ በዘይት ጠብሶ ማውጣት፡፡
- በቀረው ዘይት ሽንኩርቱን እስኪለሰልስ አቁላልቶ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ፣ የሎሚ ጭማቂ ከዓሣው ጋር አዋሕዶ ማቅረብ፡፡
ከሁለት እስከ ሦስት ሰው ይመግባል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)