Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሐዋሳ ተካሄደ

የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሐዋሳ ተካሄደ

ቀን:

ሠላሳ ሦስተኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው ውድድር በወንዶች ክብረወሰን ተሻሽሎበታል፡፡

ለዓለም አቀፍ ተሳትፎዎች ብቸኛው ውድድር የሆነው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን በቀጣይ ታዋቂ አትሌቶች ሙሉ በሙሉ የሚሳተፍበት እንደሚሆንና ለዚያም ጠንካራ ሥራ እንደሚጠብቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ውድድሩ ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለክለቦችና በግል ለሚወዳደሩ የማራቶን አትሌቶች ዕድል መፍጠሪያና እግረ መንገዱንም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሌሎች አገሮች ተሳታፊዎችን ቁጥር ለመጨመር ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን የፌዴሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጂሎ አስረድተዋል፡፡

የሽልማት መጠኑን ከፍ ያደረገው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ለአትሌቶቹ ከሚፈጠረው የውድድር አጋጣሚ ባሻገር ለከተማው የቱሪስት ፍሰትን የመጨመር ዕድል እንዳለውም ተገልጿል፡፡

ከ500 በላይ አትሌቶችን ያሳተፈው 33ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን 20 ክለቦች፣ ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደርና ግል ተሳታፊዎች ተካፍለውበታል፡፡

በወንዶች ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብርሃኑ ተሾመና ደረሰ ረታ 2 ሰዓት 12 ደቂቃ 20 ሰከንድ እና 2 ሰዓት 12 ደቂቃ 52 ሰከንድ አጠናቀው አንደኛ ሁለተኛ ወጥተዋል፡፡ ስንታየሁ ለገሰ ከፌዴራል ፖሊስ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ከ30 ሺሕ እስከ 16 ሺሕ ብር ድረስ  የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በሴቶች ሙሉ ሀብት ፀጋ ከፌዴራል ፖሊስ 2 ሰዓት 42 ደቂቃ 05 ሰከንድ አንደኛ፣ ተስፋነሽ መርጋ ከፌዴራል ፖሊስ 2 ሰዓት 42 ደቂቃ 00 ሰከንድ ሁለተኛ፣ እንዲሁም አበሩ መኩሪያ ከኦሮሚያ ፖሊስ 2 ሰዓት 43 ደቂቃ 03 ሰከንድ በመግባት ተመሳሳይ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በወንዶች አምና የተያዘው ሰዓት ዘንድሮ 2 ደቂቃ፣ 13 ሰከንድ ተሻሽሎ ተመዝግቧል፡፡

በሻምበል አበበ ቢቂላ የተሰየመው ይህ የማራቶን ውድድር የተጀመረው በ1976 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን፣ በየዓመቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በዚህ ማራቶን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የውጭ አገር አትሌቶች ይሳተፉ እንደነበርና ስያሜውም የአበበ ቢቂላ ዓለም አቀፍ ማራቶን ውድድር ይባል እንደነበር፣  ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ግን ውድድሩ አገራዊ መልክ ብቻ እንዲይዝና ስያሜውም የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሚል መሰየሙን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...