Saturday, January 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአሜሪካ ልምድ ያላቸውን ዲፕሎማት ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት አጨች

አሜሪካ ልምድ ያላቸውን ዲፕሎማት ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት አጨች

ቀን:

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልምድ ያላቸውን ዲፕሎማት ማይክል ሬይነርን ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት ዕጩ አድርገው አቀረቡ፡፡ ሹመታቸው በሴኔት በቅርብ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡

ተሿሚው በሚቀጥሉት ወራት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ፣ ተሰናባቹ የኤምባሲው ጊዜያዊ ኃላፊ ፒተር ቭሮማን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በግንቦት ወር በፕሬዚዳንት ትራምፕ በዕጩነት የተመረጡት ሬይነር ቀደም ባሉ ዓመታት በአፍጋኒስታን፣ በቤኒን፣ በጂቡቲና ከስድስት በላይ በሚሆኑ የአፍሪካ አገሮች በአምባሳደርነትና በዲፕሎማትነት አገልግለዋል፡፡

ከቀድሞዋ አምባሳደር ፓትሪሽያ ሃስላክ ስንብት በኋላ ላለፉት አሥር ወራት የኤምባሲው ጊዜያዊ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉት ቭሮማን አገልግሎታቸውን አጠናቀው ከመሰናበታቸው በፊት በተለይ ከሪፖርተር ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ለኢትዮጵያ የተመደቡት አዲሱ ዕጩ አምባሳደር የካበተ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት ናቸው፡፡ የትራምፕ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በመጀመሪያው ዙር ቅድሚያ በመስጠት ለአምባሳደርነት ዕጩዎችን ካቀረበላቸው አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን አስረድተዋል፡፡

የአዲሱን አምባሳደር ሹመት በተመለከተም፣ “በአዲሱም አስተዳደርም ቢሆን አሜሪካ ለኢትዮጵያ የተለየ ትኩረት መስጠቷን ማሳያ ነው፤” በማለት አወድሰውታል፡፡ የሴኔቱ ልዩ ኮሚቴ የሬይነርን ዕጩነት በቀናት ውስጥ እንደሚያፀድቀው የሚጠብቁት ቭሮማን፣ ዕጩው የኢትዮጵያ መንግሥትን ይሁንታ ማግኘታቸውንም አክለዋል፡፡

በተያያዘ የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ለአገሮች በምታደርገው የቁሳቁስ ዕርዳታም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ በተመለከተ ያስታወቀው የወጪ ቅነሳ፣ ኢትዮጵያ በምታገኘው ዕርዳታ ላይም ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ቭሮማን ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን  ይበልጥ በመጪው የአገሪቱ የበጀት ዓመት የሚታይ ይሆናል ያሉት ቭሮማን፣ አሁንም ቢሆን አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ ያልተቋረጠ መሆኑን፣ በተለይ በሰብዓዊ ዕርዳታ በኩል አሁንም ድረስ የኢትዮጵያ ትልቋና ቀዳሚዋ አጋር መሆኗን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

በተለይም በድርቅ ለተጠቁ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደረገው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ፣ የጤና ነክ ጉዳዮችና የልማት ሥራዎችን በተመለከት የሚደረገው ዕርዳታ አዲሱም መንግሥት ድጋፉን እየቸረው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ራሳቸው ቭሮማን በአሜሪካ በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው የግሎባል ጤና ጉዳዮች ስብሰባ ላይ በተሳተፉበት ወቅት፣ ከአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ የሚደረገውን ዕርዳታ በተመለከተ መወያየታቸውንና ኃላፊዎችም እንደሚደግፏዋቸው ቃል የተገባላቸው መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በቀድሞዎቹ የአሜሪካ መሪዎች በተለይ በጆርጅ ቡሽና በባራክ ኦባማ ሲደገፉ የቆዩት ጤና ነክ ፕሮጀክቶችን፣ አዲሱ አስተዳደር እንደተደሰተባቸውና ድጋፉንም ለመቀጠል ፍላጎት ማሳየቱን ቭሮማን ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...