Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየፖለቲካ ፓርቲዎች በአወዛጋቢ ሕጎችና በብሔራዊ መግባባት ላይ ድርድር ሊጀምሩ ነው

  የፖለቲካ ፓርቲዎች በአወዛጋቢ ሕጎችና በብሔራዊ መግባባት ላይ ድርድር ሊጀምሩ ነው

  ቀን:

   ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግና አገር አቀፍ ፓርቲዎች ብሔራዊ መግባባት፣ አወዛጋቢ ሕጎች፣ የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና የፍትሕ አካላት ተቋማትን ጨምሮ በ12 አጀንዳዎች ላይ የሚያደርጉት ድርድር ዝርዝር ፕሮግራም ተለይቶ ለፓርቲዎቹ ተሰጠ፡፡ ድርድሩ ከዓርብ ሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

  ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሚደራደሩባቸው አጀንዳዎች የመጀመሪያው የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/99 ሲሆን፣ ሰባት የመደራደሪያ ጊዜያት ተቀምጠውለታል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 662/2002 ሁለተኛና ሦስተኛ ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት የመደራደሪያ ጊዜ ተቀምጦላቸዋል፡፡

  በአራተኛነት የተቀመጠው የፀረ ሽብርተኛነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የሚመለከት ሲሆን፣ አሥር የመደራደሪያ ጊዜያት እንደተመደቡለት ታውቋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ፣ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ተቋማት አደረጃጀትና አፈጻጸም፣ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት የመደራደሪያ ጊዜያት እንደተመደቡላቸው ታውቋል፡፡ የፍትሕ አካላት አደረጃጀት አዋጅና አፈጻጸም አሥር የድርድር ጊዜያት፣ ዜጎች በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎች የመዘዋወር፣ የመኖርና ንብረት የማፍራት የሕግ ማዕቀፍና የታክስ ሥርዓት ሕግ እያንዳንዳቸው ስምንት ስምንት የመደራደሪያ ጊዜያት ተመድቦላቸዋል፡፡ የመጨረሻው አጀንዳ ብሔራዊ መግባባት ደግሞ አሥር የመደራደሪያ ጊዜያት እንደተመደቡለት ታውቋል፡፡

  በአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሠራር ደንብ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (5 እና 7) መሠረት ከመኢአድ፣ ኢዴፓና ኢራፓ የተመረጡት አደራዳሪዎች ለተደራዳሪ ፓርቲዎች ሐምሌ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በላኩት ደብዳቤ እንዳስታወቁት፣ በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ ዓርብ ሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ውይይት እንደሚያደርጉም ተገልጿል፡፡

  ለ12ቱም አጀንዳዎች ተደራዳሪ ፓርቲዎች የጽሑፍ ማቅረቢያ ጊዜ እንደ አጀንዳዎቹ በሦስትና በአምስት ቀናት ውስጥ የመደራደሪያ ነጥቦቻቸውን በጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡ አደራዳሪዎቹ የቀረቡላቸውን የጽሑፍ መደራደሪያ ነጥቦች በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚያሠራጩም ከወጣው የጊዜ ሰሌዳ ለማወቅ ተችሏል፡፡

  ተደራዳሪ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ፣ ኢዴፓ፣ መኢብን፣ መኢአድ፣ ኢሠዴፓ፣ የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ፣ ኢዲሕ፣ መኢዴፓ፣ ኢብአፓ፣ ቅንጅት፣ ኢዴአን፣ ኢፍዴኃግ፣ መኦሕዴፓ፣ ኢራፓ፣ አትፓና አንድነት ፓርቲዎች ናቸው፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...