Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊመንግሥት ግዮን ሆቴልና የፍልውኃ አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስተዳደር እንዲተላለፉ ወሰነ

መንግሥት ግዮን ሆቴልና የፍልውኃ አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስተዳደር እንዲተላለፉ ወሰነ

ቀን:

በምሕረት ሞገስና በውድነህ ዘነበ

የፌዴራል መንግሥት ላለፉት በርካታ ዓመታት በሥሩ የቆዩትን ግዮን ሆቴሎች ድርጅትና የፍልውኃ አገልግሎት ድርጅት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የእንጦጦና አካባቢው የቱሪስት መዳረሻ ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ባዘጋጀው የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ለመምከር ሰኔ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ በጠራው ስብሰባ፣ መንግሥት ግዮን ሆቴልና የፍልውኃ አገልግሎት ድርጅት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሰጥ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ሁለቱ ተቋማት ለአዲስ አበባ ተላልፈው እንዲሰጡ የሚያደርገውን ደብዳቤ ተቀብያለሁ፤›› በማለት ከንቲባ ድሪባ ደስታ በተሞላበት ስሜት ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ወይም 25 ዓመታት የሚመራበት አሥረኛው ማስተር ፕላን ሲዘጋጅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይህ ማስተር ፕላን የአዲስ አበባን መካከለኛ ክፍል ሰፋፊ ይዞታ ይዘው የሚገኙትን ታሪካዊ ተቋማት አንድ ላይ በማዳበል፣ ትልቅ ማዕከላዊ ፓርክ መገንባት እንዳለበት ምክረ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡

በተለያዩ መድረኮች በተደረጉ የማስተር ፕላን ውይይቶች ይህ ሐሳብ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በተለይ በግዮንና በፍልውኃ ይዞታዎች ጉዳይ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ሲነጋገር መቆየቱን ከንቲባ ድሪባ ተናግረዋል፡፡  

በመጨረሻ የፌዴራል መንግሥት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ሥር እየተዳደሩ የሚገኙትን ተቋማት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በየካቲት 2009 ዓ.ም. ባወጣው ሰነድ፣ ግዮን ሆቴሎች ድርጅትና የፍልውኃ አገልግሎት ድርጅት ወደ ግል እንደማይተላለፉ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ግዮን ሆቴል ለበርካታ ጊዜያት ወደ ግል ይዞታ ለማስተላለፍ ቢሞከርም፣ ሙከራው ግን ውጤታማ ባለመሆኑ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በዚህ ምክንያትም መንግሥት ግዮንን ወደ ግል የማስተላለፉ ሐሳብ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ የፍልውኃ አገልግሎት ግን ጨረታ ወጥቶለት አያውቅም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ አሁን ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማቲዮስ አስፋው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አካባቢው ለማዕከላዊ ፓርክ እንዲሆን በማስተር ፕላኑ ታቅዷል፡፡

‹‹ግዮን ሆቴል፣ የፍልውኃ አገልግሎት ድርጅትና በሥሩ የሚገኘው ፊንፊኔ የምግብ አዳራሽ፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት (ኢዮቤልዩ)፣ መስቀል አደባባይና ኤግዚቢሽን ማዕከል ማዕከላዊ ፓርክ ሆነው በማስተር ፕላኑ ታቅደዋል፤›› ሲሉ አቶ ማቲዮስ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...