Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቤቶች ኮርፖሬሽን የግል መኖሪያ ቤት ያላቸውን ከመንግሥት ቤቶች እያስለቀቀ ባለመሆኑ ተወቀሰ

ቤቶች ኮርፖሬሽን የግል መኖሪያ ቤት ያላቸውን ከመንግሥት ቤቶች እያስለቀቀ ባለመሆኑ ተወቀሰ

ቀን:

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መኖሪያ ቤት እያላቸው በመንግሥት የኪራይ ቤቶች የሚኖሩትን ተከታትሎ እያስለቀቀ ባለመሆኑ ተወቀሰ፡፡

ወቀሳውን ያቀረበው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም ኮርፖሬሽኑ ተመሳሳይ ትችት በፌዴራል ዋና ኦዲተር ቀርቦበታል፡፡

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች አንዳንድ ተከራዮች የግል ቤት ሠርተው በመንግሥት ቤት እየኖሩ ቢሆንም ተቋሙ ተከታትሎ እያስለቀቀ አለመሆኑን በመጥቀስ ወቀሳ አቅርቧል፡፡

የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸው ዜጎች በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ቢገነዘብም፣ የግል ቤት እያላቸው በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ተከራዮችን በማስለቀቅ የተቸገሩ ዕድሉን እንዲያገኙ አለማመቻቸቱን፣ ዋና የሕዝብ ዕንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዝያ አህመድ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የቤት ኪራይ ተመን መመርያ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ቢሆንም፣ መመርያው በጥናት ላይ ተመሥርቶ መቼና እንዴት ተመንና ኪራይ እንደሚወጣና እንደሚጨምር በዝርዝር የሚያመለክት ነገር አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡

ተመሳሳይ ወቀሳ ከዓመት በፊት በፌዴራል ዋና ኦዲተር ቢቀርብበትም ችግሮቹ እንዳልተፈቱ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ሪፖርት ያሳያል፡፡ ይህንንና መሰል ችግሮችን ለመፍታትና ተጨማሪ ቤቶችን በመገንባት ለመንግሥት እንዲያቀርብ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ተቋም በቅርቡ በአዋጅ እንዲፈርስ ተደርጎ፣ ሀብትና ንብረቱ እንደ አዲስ ለተቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መተላለፉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...