Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀች

ቀን:

  • ፌዴሬሽኑ 857 ሺሕ ብር ሸልሟል

በሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ የተዘጋጀው 13ኛው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለፈው እሑድ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በታሪክ የመጀመርያ የሆነውን የሜዳሊያ ቁጥር አስመዝግባ በበላይነት አጠናቀቀች፡፡

ከናይጄሪያ በስተቀር ሁሉም የአፍሪካ አገሮች በተሳተፉበት የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያ 13 የወርቅ፣ 13 የብርና 12 የነሐስ በድምሩ 38 ሜዳሊያዎች አስመዝግባለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ 12 የወርቅ፣ አራት የብርና በአንድ የነሐስ በምድሩ 17 ሜዳሊያ ሁለተኛ፣ አስተናጋጇ አልጄሪያ ደግሞ አራት የወርቅ፣ ስምንት የብርና ስምንት የነሐስ በምድሩ 20 ሜዳሊያ አስመዝግባ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ምሥራቅ አፍሪካዊት የአትሌቲክሱ ኃያል ኬንያ በአጠቃላይ በአሥር አትሌቶች ተወክላ አራት የወርቅ፣ አራት የብርና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአሥር ሜዳሊያ አራተኛ በመሆን ስታጠናቅቅ፣ ከተሳታፊ አገሮች መካከል 14 አገሮች በሻምፒዮናው የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በሁለቱም ጾታ በ49 አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ፣ ቀደም ሲል በማትታወቅባቸው ርቀቶች ማለትም 100 ሜትር ቀጥታ ወንዶችና ሴቶች፣ 100 ሜትር መሰናክል ሴቶች፣ 400 ሜትር ወንዶችና ሴቶች፣ 400 ሜትር መሰናክል ወንዶች፣ 800 ሜትር ሴቶች፣ 1,500 ሜትር ወንዶች፣ 3,000 ሜትር ሴቶችና 3,000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ውጤት ማስመዝገብ መቻሏ ከዚህ በፊት የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ ባልተሠራባቸው የውድድር ዓይነቶች ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ከተቻለ በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም በዘርፉ የአገሪቱ ተሳትፎ የጎላ እንደሚሆን አመላካች ስለመሆኑ ጭምር እየተነገረ ይገኛል፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት በግብፅ ካይሮ አድርጎ አልጄሪያ አልጀርስ የገባው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ በትራንዚት ምክንያት ለሰባት ሰዓታት ያህል በካይሮ ኤርፖርት ለመቆየት ተገዶ እንደነበርም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ እዚህ ላይ የአትሌቶቹን ገድል የሚያጎላው ደግሞ ውጤቱ ብቻ አልነበረም፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ አትሌቶቹ ከአልጀርስ ከተማ ሻምፒዮናው ወደተስተናገደበት ቴሌመንሰን ከተማ ለመድረስ ከ600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት በአውቶቡስ ተጉዘው መድረሳቸውና ይህንኑ የጉዞ ውጣ ውረድ ምክንያት ሳያደርጉ በቁርጠኝነት ከአፍሪካ ቁንጮ ሆነው የሜዳሊያ ሰንጠረዡን መቆጣጠራቸው ውጤቱን አስገራሚ እንደሚያደርገው ተመልክቷል፡፡

ሜዳሊያ ያስመዘገቡ አትሌቶች

በወንዶች ታከለ ንጋቱ 3,000 ሜትር መሰናክል 8፡31.36 ወርቅ፣ ዮሐንስ አላጋው 10,000 ሜትር እርምጃ 44፡ 43.47 ወርቅ፣ ወገን ጢቻ 400 ሜትር 47፣65 ወርቅ፣ ወልዴ ቱፋ 1,500 ሜትር 3፣ 44፣ 39 ወርቅ፣ መርዕድ ዓለሙ 400 ሜትር መሰናክል 53፡51 ወርቅ፣ ሰሎሞን ባረጋ 5,000 ሜትር 13፡51.43 ወርቅ፣ በ4X100 ሜትር ኤፍሬም መኰንን፣ ወገን ጢቻ፣ አሸናፊ ደበሌና አብዱራህማን አብደላ 3፡11.89 ወርቅ ያገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡

በሴቶች ትግስት ከተማ 800 ሜትር 2፡05.85 ወርቅ፣ ፍሬሕይወት ወንዱ 400 ሜትር 54፡43 ወርቅ፣ መስከረም ማሞ 5,000 ሜትር 15፡37.13 ወርቅ፣ አያልነሽ ደጄኔ 10,000 ሜትር እርምጃ 52፡14.43 ወርቅ፣ መቅደስ አበባ 3,000 ሜትር መሰናክል 10፡11.30 ወርቅ፣ በ4X10 ሜትር ማህሌት ፍቅሬ፣ ሽምኮራ መኰንን፣ ዝናሽ ተስፋዬና ፍሬሕይወት ወንዴ 3፡48.19 ወርቅ ያስመዘገቡ አትሌቶች ናቸው፡፡

የብር ሜዳሊያ ያስመዘገቡ ወንዶች ተስፋዬ ድሪባ 3,000 ሜትር መሰናክል 8፡33.67፣ ግዛቸው ኃይሉ 10,000 ሜትር 29፡52.20፣ አዲር ጉረ ሱልስ ዝላይ 16፡65፣ ታደሰ ለማ 800 ሜትር 1፡48.76፣ ዴቪድ ዴንግ ከፍታ ዝላይ 1.90 ሜትር፣ ተስፋሁን አካልነው 5,000 ሜትር 13፡52.91 ናቸው፡፡

በሴቶች አጂዳ ኡመር አሎሎ ውርወራ፣ 11፡94 ሜትር፣ ማህሌት ፍቅሬ 400 ሜትር 56፡45፣ ዳሜ አቡ 400 ሜትር መሰናክል 1፡01.18፣ ጽጌ ድጉማ 200 ሜትር 24፡71፣ ፋንቱ ወርቁ 1,500 ሜትር 4፡30.76 እና ማዕቱ ከተማ 3,000 ሜትር መሰናክል 10፣ 12፣ 83 ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገቡ ወንዶች፣ ኢብራሂም ጀማል 110 ሜትር መሰናክል 14፡50፣ አዲስ ግርማ 800 ሜትር 1፡49.15፣ ከረዩ ቡላላ ጦር ውርወራ 58፡49፣ ታደሰ ተስፋሁን 10,000 ሜትር 30፡13.95፣ ምጋ አሎሎ ውርወራ 17፡02 ሜትር ናቸው፡፡

በሴቶች አልማዝ ሳሙኤል 1,500 ሜትር 4፡31.59፣ ቃልኪዳን ክንፈ 5,000 ሜትር 15፡13.65፣ ኤቢሴ ከበደ 100 ሜትር 12፡45፣ ገበያነሽ ጉደታ 100 ሜትር መሰናክል 15፡03 እና መሰሉ በርሔ 3,000 ሜትር 9፡28.10 ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በ13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳታፊው ቡድን ብሔራዊ ፌዴሬሽን ከ857 ሺሕ ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡

ፌደሬሽኑ ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በአራራት ሆቴል ባዘጋጀው የሽልማት ሥነ ሥርዓት የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች 17 ሺሕ፣ ለብር ሜዳሊያ 13 ሺሕ እና ለነሐስ ሜዳሊያ ደግሞ 9,500 ብር ለእያንዳንዳቸው የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ አሠልጣኞችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለልዑካን ቡድኑ አባላት እንደየደረጃቸው ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ማበርከቱ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡  

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...