Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  «ምን ይባላል?»

  ትኩስ ፅሁፎች

  ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው ደብረ ብርሃን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ መንደር ጥሶ የገባው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ

   *****

  የዛፍ ላይ ፍየሎች

  ፍየል የቤት እንስሳ ከብት ነው፡፡ በምድረ በዳ ካለው የዱር ፍየልም ይለያል፡፡ በተረትና ምሳሌም ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ፤ ሜ ባልኩ ፍየል ከፈልኩ፤ የፍየል ዓይን ቅጠል የነብር ዓይን ወደ ፍየል ወዘተ ይጠቀሳል፡፡ ቆላማ አካባቢ የማይጠፉት ፍየሎች ተንጠላጥለው ቅጠላ ቅጠል በመበጠስ መመገባቸው የተለመደ ነው፡፡ በአስቸጋሪና አዳጋች ቦታዎች፣ ገደላማ ሥፍራዎች ተንጠላጥለው የዕለት መኖአቸውን ለመቋደስ አይሰንፉም፡፡

  መሰንበቻውን ከወደ ሞሮኮ ፍየሎችን በተመለከተ የተሰማው ለየት ያለ ነገር አለው፡፡ እንደ አትላስ ኦብስኩራ ዘገባ፣ በደቡብ ምዕራባዊ ሞሮኮ ግዛት የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎ በተከሰተው ድርቅ የምግብ እጥረት ሰለባ የሆኑት ፍየሎች መላ የመቱት የአርጋን ዘይት የሚገኝበት አገር በቀል ዛፍ ላይ እንደ ጦጣ በመንጠላጠል መቀነጣጠብና መቀማመስ ነበር፡፡

                                *****

  እንጂ

  ማፍቀር አይደለም

  ድንቁ

  እንጂ

  አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ

  መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ

  እንጂ እውቀቱ

  ሲፈቀሩ ፍቅር መሰማቱ

  እውቀት አይደለም

  ቁም ነገሩ

  ጉዱ

  እንዳወቁ ማወቁ

  • ሰሎሞን ዴሬሣ ‹‹ዘበት እልፈቱ ወለሎታት››

  ******

  ሼርሎክ ሆልምስ እና ዶክተር ዋትሰን

  ሼርሎክ ሆልምስ እና ዶክተር ዋትሰን ዝነኛ የመጽሐፍት ገጸ-ባህርያት ናቸው። ከ1887 ጀምሮ ሼርሎክ ሆልምስን ዋና ገጸ-ባህሪ ያደረጉ ሀምሳ ስድስት አጭር ልብወለዶችና አራት ረጅም ልብወዶች በስኮትላንዳዊው ሀኪምና ደራሲ በሰር አርተር ኮናን ዶይል ተጽፈዋል። ከነዚህ ውስጥ ከአራቱ በስተቀር ሁሉም የሚተረኩት በሆልምስ የልብ ጓደኛ ዶክተር ዋትሰን ነው። ሆልምስ በአመክኖያዊ አስተሳሰቡና አካባቢውን በሚገባ አስተውሎ ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ በመድረስ ይበልጥ ይታወቃል።

  አንድ ቀን ሆልምስ እና ዋትሰን ሽርሽር ይሄዳሉ። እራታቸውን በደንብ ከበሉ በኋላ ሁለቱም በየድንኳናቸው ተከተው ለጥ ብለው ተኙ።

  ከጥቂት ሰዓታት እንቅልፍ በኋላ፡ ሆልምስ ይነቃና ጓደኛውንም ይቀሰቅሰዋል።

  “ዋትሰን!እስኪ ወደ ላይ ተመልከት!ምን ይታይሀል?”

  “ሆልምስ!በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከክዋክብት ይታዩኛል።”

  “ታዲያ ከዚህ ምን ተረዳህ?” ዋትሰን ለጥቂት ደቂቃ ካሰበ በኋላ
  “በክዋክብት ጥናት መነጽር ካስተዋልነው፡ በሚሊየን የሚቆጠሩ ጋላክሲዎችና በቢሊየን የሚቆጠሩ ፕላኔቶች እንዳሉ ይነግረናል። በኮከብ ቆጠራ አስተምሕሮ ካነጠርነው ደግሞ ሳቱርን በእንቅስቃሴ ዑደቷ ሊዎ ላይ እንደምትገኝ ያስታውሰናል።ሰዓቱን ለማወቅ ከተጠቀምንበት ለዘጠኝ ሩብ ጉዳይ መሆኑን ይነግረናል። የአየር ንብረቱን ለመተንበይ ካዋልነው ፡ ነገ ብራ ቀን ሆኖ እንደሚውል ይጠቁመናል። በሀይማኖት ትምሕርት መሰረት ደግሞ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ መሆኑን እና እኛም ደቃቅና ከቁጥር የማንገባ የህዋው አካል መሆናችንን ያበስረናል . . . ላንተስ ምን ይነግርሀል ሆልምስ?“

  ሆልምስ ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አለና ”ዋትሰን! አንተ የማትረባ! ድንኳናችን መሰረቁን ምንም አላስተዋልክም!“

  ይህቺ አጭር ቀልድ፡ ብዙ ቁም-ነገር የያዘች ናትና እንዲህ ለማለት ተፈልጎ ነው እያልኩ በመተንተን አልገድባችሁም።

  • የቴዎድሮስ ሸዋንግዛው ገጽ

  *****

  ‹‹እባቡን ከማስቆጣትህ በፊት…››

  ተግባራዊ ጥበብን የሚያጎሉ በርካታ ምሳሌያዊ አነጋገሮች የአስተዋይነትንና የአርቆ ተመልካችነትን አስፈላጊነት በጥሩ ሁኔታ ይገልጻሉ። የሚያደርጋቸው ነገሮች ምን መዘዝ እንደሚያስከትሉ ሳያመዛዝን አንድ ነገር ውስጥ ዘው ብሎ የሚገባ ግድየለሽ ሰው ከሚከተለው ተረት ጥሩ ምክር ያገኛል። “እባቡን ከማስቆጣትህ በፊት መውጫህን አሰናዳ።” መጥፎ አዝማሚያ የሚታይበት ልጅ ያለው ወላጅ የሚከተለውን ተረት ልብ ማለት ያስፈልገዋል።

  “የሚያድግ ቅርንጫፍ ዓይንህን ሊወጋ ከተቃረበ ንቀለው እንጂ አትመልምለው።” አዎን፣ ማንኛውም መጥፎ ባሕርይ ገና በእምቡጥነቱ መቆረጥ ወይም መነቀል ይኖርበታል እንጂ አቆጥቁጦ ችግር እስኪፈጥር ድረስ መታለፍ አይኖርበትም።

  • (ንቁ!—2003)

   

   

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች