Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ወልዋሎ ዓዲግራትና ጅማ ከተማ ይጋጠማሉ

  የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ወልዋሎ ዓዲግራትና ጅማ ከተማ ይጋጠማሉ

  ቀን:

  ‹‹ከፍተኛ ሊግ›› በሚል አደረጃጀት መካሄድ ከጀመረ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ ምድብ ጨዋታዎች ሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ተካሂደው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና ጅማ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

  በምድብ አንድ በመቐለ ከተማ የተገናኙት መሪው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና መቐለ ከተማ በአቻ ውጤት 1ለ1 ተለያይተዋል፡፡ በዚህ ውጤት መሠረት ወልዋሎ በ64 ነጥብ የ2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተካፋይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

  ከምድብ ሁለት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማለፍ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች በጅማና በሆሳዕና ከተሞች ተካሂደዋል፡፡

  ጅማ ከተማ በጅማ ስታዲየም ወልቂጤ ከተማን 3ለ1 ሲያሸንፍ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከሀለባ ከተማ ጋር ገጥሞ ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሠረት ጅማ ከተማ በአንደኛነት በማጠናቀቁ ለቀጣይ ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል፡፡ የዘንድሮ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማክሰኞ ሐምሌ 11 ቀን በድሬዳዋ ከተማ የሚጠናቀቅ ሲሆን የየምድቡ አንደኞች ወልዋሎ ዓዲግራትና ጅማ ከተማ ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ሁለተኞቹ መቐለ ከተማና ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ፕሪሚየር ሉጉ ሦስተኛው አላፊ ቡድን ለመሆን የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ነው፡፡

  የዘንድሮው የሊጉ ሻምፒዮና የየምድብ ጨዋታው በተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ ከብጥብጥና ሁከት አለመለየታቸው በተጫዋቾች፣ እንዲሁ በደጋፊዎች መካከል የተፈጠሩት አምባጓሮዎች ጨዋታዎችን እስከማቋረጥ ደርሰው ነበር፡፡

  ቡድኖች የጨዋታ ውጤትን በፀጋ ተቀብሎ ለሚቀጥለው ሥራቸው የሚበጀውን ማቀድ ሲኖርባቸው ለብጥብጥና ሁከት ምክንያት የሚሆኑበት ዕድል እየሰፋ መምጣቱም ታይቷል፡፡ ይኼ ጉዳይ ብሐራዊ ፌዴሬሽኑ በበላይነት እያመራቸው በሚገኙ ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በሁሉም ሊጎች እየተስተዋሉ ይገኛል፡፡ ቡድኖች ከከተማቸው ወጥተው ተጫውተው ሽንፈትን ካስተናገዱ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚስተጓጎልበት፣ ዜጎች በማንነታቸው የሚጎዱበትና ንብረት የሚወድምበት መድረክ መሆኑ ለምን የሚሉ ጥያቄዎችንም ማስነሳት ጀምሯል፡፡

  በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሁሉም የዓመቱ መርሐ ግብሮች ባብዛኛው የተጠናቀቁበት እንደመሆኑና ለሚቀጥለው ዓመት መርሐ ግብር ዝግጅት የሚጀምርበት በመሆኑ ይኼ ለእግር ኳሱ ብቻ ሳይሆን ለሰው አካልና ንብረት ውድመት ምክንያት እየሆነ ባለው ‹‹ወንዜነትና ጎጠኝነት›› ላይም የሚመለከታቸው አካላት መፍትሔ እንዲሰጡበት አስተያየት እየተሰጠበት ይገኛል፡፡

  ከእነዚህ አካላት የአንባሳውን ድርሻ የሚወስደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከመርሐ ግብር ዕጣ አወጣጥ ጀምሮ ስፖርቱ ካጋጠመው ችግር ለመውጣት ይችል ዘንድ ሥርዓቶችንና አደረጃጀቶችን፣ እንዲሁም ተጠያቂነትንና ግልጸኝነትን ማስፈን የሚችል መዋቅር በመዘርጋት ሙያዊ ብቃቱ ባላቸው ሰዎች መመራት እንዲችል መትጋትና መሥራት እንዳለበትም የሚናገሩ አሉ፡፡

  ቀጣዩ ዓመት ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የቀጣዩን አራት ዓመት የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ የሚያደርግበት እንደሚሆን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ መንግሥትና የሚመለከተው አካል ተቋሙን እንዲያስተዳድሩ ከእያንዳንዱ ክልል ለምርጫ የሚወከሉት ግለሰቦች የሙያዊ ብቃታቸው ጉዳይ እንዲታሰብበት ከወዲሁ ማሳሰቢያ እየተሰጠ ነው፡፡

  spot_img
  Previous article
  Next article
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...