Sunday, May 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከኢታኖል ድብልቅ ነዳጅ በአምስት ወራት 1.6 ሚሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉ ተነገረ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢታኖልን ከቤንዚን ጋር ማደባለቅ በድጋሚ በተጀመረ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ 1.6 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማዳን እንደተቻለ ተጠቆመ፡፡

ከማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሪፖርተር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተቋርጦ የነበረው የኤታኖልና የቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ በድጋሚ የተጀመረው በሚያዝያ 2009 ዓ.ም. መጀመርያ ላይ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ለተሽከርካሪዎች እየቀረበ ያለው ቤንዚን አምስት በመቶ ከኤታኖል ጋር የተደባለቀ ሲሆን፣ ወደፊት የኢታኖል መጠኑን ወደ አሥር በመቶ ለማድረስ ጥናት በመደረግ ላይ ነው ተብሏል፡፡

ኢታኖልን ከቤንዚን ጋር እንዲደባለቅ የሚደረግበት ዋነኛው ምክንያት የውጭ ምንዛሪን ለማስቀረት ሲሆን፣ ሌላው ምክንያት ደግሞ በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ብክለት ለመቀነስ እንደሆነ መረጃው ያመለክታል፡፡

ባለፉት አምስት ወራትም ከ1.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን እንዲሁም አምስት ሺሕ ቶን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይቀላቀል ማድረግ መቻሉን መረጃው ያስረዳል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ታስገባለች፡፡ ለዚህም 2.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአገሪቱ የቤንዚን ፍጆታ 288 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ነበር፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች