Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤን ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤን ተጠየቀ

ቀን:

  • የአቤቱታ ድምፅ መሰብሰብ ተጀምሯል

የኢትዮጵየ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድኑን እንዳፈረሰ ዜናው ከተሰማ ጀምሮ የፋይናንስ ተቋሙን ውሳኔ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ አስተያየቶች እየተደመጡ ይገኛል፡፡

ባንኩ ውሳኔውን ዳግመኛ እንዲያጤነው የሚጠይቁ አካላት፣ የድርጅቱን አካሄድ ይተቻሉ፡፡ ባንኩ ከሌሎች የእግር ኳስ ክለቦችን ዓመታዊ በጀት በመመደብ ከሚያስተዳድሩ መንግሥታዊም ሆነ የግል ተቋማት አኳያ የሚገኝበት የፋይናንስ አቅምም ሆነ ብቃት ቡድኑን ለማፍረስ ያቀረበው ምክንያት እንዲሁም ተቋሙ ካለበት ማኅበራዊ ኃላፊነት አንፃር ተገቢ እንዳልሆነም እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከዚህም ባሻገር በ2003 ዓ.ም. በሰባት የመንግሥትና የግል ባንኮች የጋራ ባለቤትነት ይተዳደር የነበረውን ይህንን ክለብ ጠቅልሎ ከተረከበ በኋላ ማፍረሱ ተገቢነቱ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች፣ ቀድሞውኑ ሲረከብ በምን አግባብነትና አኳኃን ነበር? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በማያያዝም ቡድኑን ከመበተን ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መመልከት ይገባው እንደነበርና አልያም ለሌሎች አቅሙ ላላቸውና ክለቡን ሊረከቡ የሚችሉ አካላት እንዲያስተዳድሩት ማስተላለፍ ሲገባው ከሦስት አሠርታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ እግር ኳስ ቡድን ማፍረሱ ንግድ ባንክ ላይ ጥያቄ እያስነሳም ነው፡፡

ቀድሞ የክለቡ ተጫዋቾች በአሁኑ ወቅት ደግሞ በባንኩ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታ በማገልገል ላይ የሚገኙ ተቆርቋሪዎች የባንኩ ኃላፊዎች ውሳኔያቸውን እንደገና እንዲያጤኑት የአቤቱታ ድምፅ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ‹‹መጪው ዓመት የኢትዮጵያ ከፍታ ነው›› በሚል ከነሐሴ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አሥር ቀን በመላ አገሪቱ ሲዘከር ከሰነበተው ዝግጅት መካከል ቅዳሜ ጳጉሜን 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የተዘጋጀው ስፖርታዊ ውድድር ይጠቀሳል፡፡

ዝግጀቱን አስመልክቶ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የአትሌቲክስ፣ የእግር ኳስ፣ የሌሎችም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና የክለቦች ተወካዮች በተገኙበት ሐሙስ ጳጉሜን 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚኒስቴሩ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በመድረኩ ከተነሱት ነጥቦች መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወንዶቹ የእግር ኳስ ቡድኑ ላይ የወስደውን የማፍረስ ውሳኔ አስመልክቶ፣ በተለይ ለሚኒስትሩ አቶ ርስቱ ይርዳውና ሌሎችም አመራሮች ጥያቄ ቀርቦ የሁሉም ኃላፊዎች መልስ የነበረው ድርጅቱ ውሳኔውን እንደገና ማጤን እንዳለበት የሚያሳስብ ነበር፡፡

የባንኩን ውሳኔ አስመልክቶ የመጀመርያውን ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በባንኩ ውሳኔ እጅጉን ማዘኑን ገልጸው ያከሉት፣ ‹‹አንድ ተቋም ባለው አደረጃጀትና የፋይናንስ አቅም አስተማማኝ ነኝ ሲል በብር ብቻ መሆን የለበትም፡፡ አስተማማኝነቱ የበለጠ ተቀባይነት የሚኖረው ለኅብረተሰብ የሚሰጠው ማኅበራዊ ግልጋሎት ሲታከልበት ነው፤›› በማለት ነበር፡፡

የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች ቡድን እንዲፈርስ ሲያደርግና ለዚያ ውሳኔ የደረሰበትን ዝርዝር ነገር መረዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረው፣ በጉዳዩ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጨምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ከባንኩ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ለመፍትሔው ጥረት ማድረግ እንደሚስያፈልግ አሳስበዋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ርስቱ ይርዳው በበኩላቸው፣ አሁን ባለው ተቋማዊ አደረጃጀት ቡድን ለመያዝና ለማስተዳደር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሻለ ቁመና ያለው ተቋም እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም እግር ኳሱን በባለቤትነት ከሚያስተዳድረው ብሔራዊ ፌዴሬሽን ጀምሮ የአሠራርና የአደረጀጀት ችግሮች እንኳ ቢኖሩ፣ በችግሮቹ ዙሪያ ተነጋግሮ የተሻለውን አማራጭ መሻት ሲገባ ቡድን ማፍረስ ተገቢና የሚደገፍ እንዳልሆነ የመሥሪያ ቤታቸውን አቋም ጭምር አንፀባርቀዋል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...