Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየንጉሠ ነገሥቱና የአልጋ ወራሹ ግጥሚያ

የንጉሠ ነገሥቱና የአልጋ ወራሹ ግጥሚያ

ቀን:

 የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት (1923-1967) የነበሩት አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ባንድ ወቅት በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥታቸው ከልጃቸው ልዑል አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠረጴዛ ቴኒስ ተጫውተው ሲጫወቱ፣ተመልካቾቹ እነ ልዕልት ተናኘ ወርቅ ኃይለ ሥላሴ፣ ልዕልት ሳራ ግዛው ነበሩ፡፡

***

‹‹ቴዲ አፍሮ›› በጂቡቲ

በቅርቡ የሙዚቃ አልበሙን የለቀቀው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ ዘፈኖቹ በጂቡቲ ከመሰማታቸው ባሻገር፣ በመዲናዋ አውራ ጎዳና በሪፐብሊክ መንገድ (Rue del la Republique) በሚሽከረከር አንድ ሚኒ ባስ የኋላ መስታወት ላይ ስሙ በሮማን ፊደል ‹‹TEDDY AFRO›› በሚል ተጽፎ ይታያል፡፡

የተወለድኩ ዕለት

እንደ ዘፋኝ ወፍ ነው ልቤ የሚዘፍነው

ጎጆዋም እንደ እሸት ውኃ የጠጣው፡

ልቤ የሚመስለው የበለስ ዛፍም ነው

ቅርንጫፉ ጎብጦ ፍሬው የከበደው፡

እንደ ቀንዳውጣ ቅል ልቤ አለው ድምቀት

በትፍስህት ባህር ላይ እንደሚቀዝፉት፡

ልቤ የላቀ ነው ከዚህ ሁሉ ደስታ፤

ለምን ይሆን ቢሉም፤ ፍቅሬ ወለላዬ

መጥቶልኛልና፡፡

 

 

 

ይሠራልኝ ዙፋን ከእንጭጭ ላባ ከሃር፡

በሓምራዊ ቀለም ከፈፋው በጎፈር፡

እርግቦች ጥረቡ በሓምራዊ ሮማን፤

አድምቃችሁ ሥሩ በጣዎስ መቶ ዓይን፤

በወርቅ ይሠራልኝ በብሩር ወይኖች፡

እንደ ሊሊ ብሩር ያለው ቅጠሎች፤

ለምን ይሆን ቢሉም የሕይወቴ ትውልድ ቀኑ

ስለደረሰልኝ

ፍቅሬ ወለላዬ ስለመጣልኝ፡፡

ከክሪስቲና ሮዜቲ (1830 – 1894)

ስድ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ

*****

በእሳት የተጫወቱ ለት

እሳት በአፉ ይዞ በእጅ የያዙትን ነገር በማቀጣጠል ትርዒት ማሳየት በተለያዩ ፌስቲቫሎች የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በፌስቲቫሎቹ በአፋቸው የያዙትን እሳት አመጣጥነው ካለመልቀቅም ሆነ በቂ ልምምድ ካለማድረግ ተያይዞ ትርዒተኞቹ ላይ ቃጠሎ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡ ከሰሞኑ በሩሲያዋ ኬሞሮቭ ከተማ በተከናወነ በአፍ በተያዘ እሳት ሌላ ነገር የማቀጣጠል ፌስቲቫል ሦስት ትርዒተኞች ፊታቸው በእሳት የመቃጠል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

ሚረር እንዳሰፈረው፣ በመከናወን ላይ በነበረው ፌስቲቫል ከተሳተፉት ሦስት  ትርዒት አቅራቢዎች ፊት ላይ የመቃጠል አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

*******

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሠሩበት ሻይ ቤት የቱሪስት መዳረሻ ሊደረግ ነው

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናርናድራ ሞዲ በልጅነታቸው ከአባታቸው ጋር ሆነው ሻይ የሚሸጡበት ቤት የቱሪስት መስህብ ሊደረግ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ እ.ኤ.አ. በ2014 የምረጡኝ ዘመቻ ሲያካሂዱ፣ የሻይ ሻጭ ልጅ መሆናቸውን በመጥቀስ አስተዳደጋቸው በመልካምና በሰው አክባሪነት የተሞላ እንደነበር ይናገሩ ነበር ሲል ኤምኤስኤን አስፍሯል፡፡

በቫንዳጋር የባቡር ጣቢያ አካባቢ የተሠራው ሻይ ቤት አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሥፍራውም በአቧራ የተሸፈነ ሲሆን፣ ለዕይታም አይማርክም፡፡ የባህል ሚኒስቴር እንዳለውም፣ ሻይ ቤቱን ለማደስና የቱሪስት መስህብ ለማድረግ የ15 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፏል፡፡

******

አውራ ጎዳናን ያዘጉ ዶሮዎች

በኦስትሪያ 7,000 ያህል ዶሮዎችን በየቅርጫታቸው አድርጎ ይጓዝ የነበረ መኪና በመጋጨቱ ዶሮዎቹ ከመኪናው ወጥተው መንገድ ዘግተዋል፡፡ ከ100 በላይ የድንገተኛ አደጋና የእሳት ማጥፋት ሠራተኞች በሥፍራው ደርሰው የተበታተኑ ዶሮዎችን ከመንገድ እስኪያነሱም መንገዱ ለትራፊክ ተዘግቷል፡፡ ከዶሮዎቹ የሞቱ፣ የተጎዱ ምንም ሳይሆኑ የተረፉ እንዳሉ ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡ ዕድል ከመታረድ ያዳናቸው ደግሞ ከአካባቢው ወደ ሌላ ሥፍራ በመሄድ ከመታረድ ተርፈዋል ሲል ዘገባው አስፍሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...