Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየኤሌክትሮኒክ ፊርማ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ቀን:

የኤሌክትሮኒክ መልዕክቶችን ከታለመላቸው ውጪ እንዳይጠቀሙበት ለመመስጠር (Encrypt) እና የተመሳጠሩ መልዕክቶች ትክክለኛ ባለቤትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁ ያስፈለገው በአገሪቱ የኤሌክትሮኒክስ ንግድ እየተስፋፋ በመምጣቱና የመንግሥት አገልግሎቶችም ኤሌክትሮኒክ እየሆኑ የሚመጡ በመሆኑ፣ ይህንን ሥርዓት ከሥጋት ለመጠበቅና ተዓማኒነት ያለው መረጃን ለመለዋወጥና ከዚህ በኃላም ተቀባይነት እንደሚኖረው ለማድረግ መሆኑን የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ረቂቅ ሕጉ የኤሌክትሮኒክ መልዕክቶችን ማስረጃዎች በተለይም ለንግድ ግንኙነቶችና ልውውጦች በሚውሉበት ጊዜ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ፣ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ መስጠት የሚቻልበትን ሥርዓት የሚፈቅድ ነው፡፡

- Advertisement -

በዚህም መሠረት ዋነኛው መሠረተ ልማት የክሪፕቶ መሠረተ ልማት ሲሆን፣ ይህም ሁለት ዓይነት አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ በማብራሪያው ተመልክቷል፡፡

እነዚህም የሚስጥር አገልግሎትና የዲጂታል ፊርማ አገልግሎቶች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡

የሚስጥር አገልግሎት የኤሌክትሮኒክ ግንኙነቶችን፣ መልዕክቶችን፣ ዳታዎችን ተነባቢ እንዳይሆኑ የመመስጠርና ወደነበሩበት ተነባቢ የኤሌክትሮኒክ መልዕክትነት የመመለስ አገልግሎት ነው፡፡ የዲጂታል ፊርማ አገልግሎት ደግሞ የተሳታፊዎችን ትክክለኛ ማንነት ለመለየትና ለማረጋገጥ፣ የመልዕክቶችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥና መካካድን ለማስቀረት የሚያስችል መሆኑ በማብራሪያው ተገልጿል፡፡

ረቂቁ እነዚህን አገልግሎቶች መስጠት ለሚችሉ ፈቃድ የሚሰጥ ባለሥልጣን የሚያቋቁም፣ እንዲሁም የተቆጣጣሪ ተቋም ሥልጣንና ተግባርንም አካቷል፡፡ ረቂቁ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለተጨማሪ ዕይታ ተመርቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...