Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዓረብ ባህረ ሰላጤ ቀውስ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ የሚጠበቀው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ሰኞ...

በዓረብ ባህረ ሰላጤ ቀውስ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ የሚጠበቀው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ሰኞ ይጀመራል

ቀን:

የአፍሪካ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ 29ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ታስተናግዳለች፡፡ የዓረብ ባህረ ሰላጤ ቀውስ ላይ የአፍሪካ መሪዎች ውሳኔ እንደሚያሳልፉም ይጠበቃል፡፡

ማክሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በየአገሮቹ ቋሚ መልዕክተኞች የተጀመረው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ፣ ሰኞና ማክሰኞ ደግሞ የአገሮችን መሪዎች እንደሚያገናኝ የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በኳታርና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተፈጠረው ግጭትና አገሮቹ የተከተሉት የተለያዩ የአሠላለፍ አጋርነቶች የአፍሪካ አገሮች ለሁለት እየከፈሉ ከመምጣታቸው አኳያ፣ ጉባዔው በዓረብ ባህረ ሰላጤ ቀውስ ላይ የአኅጉሩን አቋም ለመወሰን እንደሚውል ይጠበቃል፡፡

እስካሁን በሳዑዲ ዓረቢያ ጫና ስምንት የአፍሪካ አገሮች ከኳታር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡ ሽብርተኛ ቡድኖችን በገንዘብ ትረዳለች በማለት ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ ባህሬንና ግብፅ ከኳታር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከሦስት ሳምንት በፊት ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡

ከኳታር ጋር ግንኙነታቸውን ካቋረጡት አገሮች መካከል አንዷ ጂቡቲ ስትሆን፣ ኳታር በኤርትራና በጂቡቲ ድንበር የነበራትን ወታደራዊ ካምፕ ለቃ ወጥታለች፡፡ ይኼንኑ ቦታ ለመያዝ ኤርትራና ግብፅ ያሳዩት ፍላጎት ለጉባዔው አስተናጋጅ ኢትዮጵያ የሥጋት ምንጭ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ በዚሁ ቀውስ ጉዳይ ላይ አቋም ወስዳ ከአንዳቸውም ጋር ያልወገነች ሲሆን፣ ሁለቱ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ግንኙነታቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ጥረት እያደረገች መሆኗን አስታውቃለች፡፡

በ29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ 24 ያህል የአፍሪካ አገር ፕሬዚዳንቶች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሬዚዳንቶች መካከልም የዚምባቤ ፕሬዚዳንት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ፣ የናይጄሪያ ሙሐመድ ቡሃሪ፣ የላይቤሪያዋ ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ፣ የሱዳን ኦማር ሐሰን አል በሽር፣ የቻድ ኢድሪስ ዳቢ፣ የኡጋንዳ ዮዌሪ ሙሴቬኒና ሌሎች  መሪዎች እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በ29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የግብፅ ሸሪፍ እስማኤልና የሞዛምቢክ ካርሎስ አጉስቲም እንደሚታደሙ ታውቋል፡፡ የስዋዚላንዱን ንጉሥ ጨምሮ ሌሎች አራት የአፍሪካ አገሮች ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከአፍሪካ አገሮች ውጪም የፍልስጤም ራስ ገዝ አስተዳደር ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ በጉባዔው እንደሚታደሙ ተጠቁሟል፡፡

29ኛ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ‹‹ሀርነሲንግ ዘ ዴሞግክራፊክ ዲቫይድድ ስሩው ኢንቨስትመንትስ ኢን ዘ ዩዝ›› በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣  ከዋና ዋና አጀንዳዎች መካከልም በአፍሪካ ያለውን የፀጥታና የአሸባሪነት ሁኔታ፣ የአጀንዳ 2063 አፈጻጸም፣ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎና የአቻ ለአቻ ጋብቻ በአፍሪካ ምን እንደሚመስል፣ እንዲሁም የቀጣዩ ዓመት የኅብረቱን በጀት ማፅደቅ ዋነኛዎቹ የመወያያ አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ አጀንዳዎች በተጨማሪ የአፍሪካ ኅብረት ያለበትን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ሲባል ተቋቁም የነበረውንና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የሚመሩት ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርት እንደሚያዳምጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በፖል ካጋሜ መሪነትና በሚስተር ዶናልድ ካቤሩካ ጸሐፊነት የአፍሪካን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የተቋቋመው ይህ ኮሚቴ፣ አዳዲስ ሥልቶችንና አሠራሮችን በማመንጨት አፍሪካ ካለባት ችግር ለመውጣት የሚያስችል ዕቅድ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በፊት የአፍሪካን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት ሲባል ወደ አፍሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የ0.2 በመቶ ቀረጥ ለማስከፈል ምክረ ሐሳብ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ከሚያነሳቸው ሌሎች ጉዳዮች መካከል በዓረብ ባህረ ሰላጤ አገሮች፣ መካከል ስለተፈጠረው ችግር፣ አፍሪካውያን ችግሩን እንዴት መፍታት እንዳለባቸው የመፍትሔ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት በሌላው የመወያያ አጀንዳ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሄድ የነበረውን የመሪዎች ጉባዔ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ምክረ ሐሳብ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንደሚታወቀው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በጥርና በሐምሌ ወር እንደሚያካሂድ ይታወቃል፡፡ ዘወትር በጥር ወር የሚካሄደው የመሪዎች ጉባዔ በአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፣ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ግን ጉባዔው የት አገር መካሄድ እንዳለበት ክርክር ሊያስነሳ  እንደሚችል ለአፍሪካ ኅብረት ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሚካሄደውን ጉባዔ ሌሎች አገሮች እንደሚያስተናግዱት ቢጠበቅም፣ በገንዘብና በሌሎች ችግሮች ምክንያት አስተናጋጅ አገር በመጥፋቱ ኢትዮጵያ ለማስተናገድ መገደዷን የኅብረቱ ምንጮች ለሪፖርተር ጠቁሙዋል፡፡

መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የሚያርፉባቸው ባለ ኮከብ ሆቴሎች መለየታቸውን የተናገሩት አቶ መለስ፣ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና ላይ እንደምትገኝም ገልጸዋል፡፡ የትራንስፖርት ዝግጅት፣ የከተማዋ ውበትና ፅዳት፣ የአየር መንገድና የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች በሙሉ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...