Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዒላማ ተኩስ ፌዴሬሽን ሊቋቋም ነው

የዒላማ ተኩስ ፌዴሬሽን ሊቋቋም ነው

ቀን:

  • ስፖርቱ አገሪቱን በዓለም አቀፍ መድረክ የመወከል አቅም እንዳለው ተነግሯል

በዓለም የስፖርቶች ጅማሮ መነሻው ወታደራዊ ተቋማት በዋናነት እንደሚጠቀሱ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ የማራቶን ሩጫ ውድድር መሠረት ተደርጎ የሚነገረው ግሪካዊ ወታደር ፌዲፒደስ አገሩ ግሪክ የማራቶን ጦርነትን ማሸነፏን ለማብሰር የተጓዘውን ርቀት በመውሰድ መሆኑ ለዚህ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ምንም እንኳ እንደማራቶን ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም በተለይም በአሁኑ ወቅት በዓለም ለሚታወቁት አብዛኛዎቹ ስፖርቶች በወታደራዊ ተቋማት የሚዘወተሩ መሆናቸው ይታመናል፡፡ ከነዚህ ስፖርቶች አንዱና ዋነኛ ሆኖ በብዙ አገሮች እየተዘወተረ የሚገኘው ደግሞ የዒላማ ተኩስ ውድድር ተጠቃሽ ነው፡፡

ስፖርቱ በኢትዮጵያ ይህንን ያህል ዕውቅና ባይኖረውም በአገሪቱ በሠራዊቱ ተቋማት ዘንድ ግን ዓመታዊ መርሐ ግብር ተይዞለት እንደሚዘወተር ይነገራል፡፡ ስፖርታዊ ውድድሩም ቀደምት ታሪክ ያለው መሆኑም ባለሙያተኞች ይናገራሉ፡፡ የአገሪቱ መከላከያ አደረጃጀቱም ሆነ አኗኗሩ ለስፖርቱ ምቹ እንደሆነና በቅርቡም በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ፌዴሬሽን ለመመሥረት መቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንቦች የመከላከያ ተቋማት ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ መሆኑ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ታምራት በቀለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እንደ ዋና ጸሐፊው የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋማት ለዒላማ ተኩስ ውድድር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ለብዙ ስፖርቶች እዚህ ደረጃ መድረስ የጎላ ድርሻ ያላቸው ናቸው፡፡

ከአትሌቲክስ ባሻገር የዒላማ ተኩስ ለአገሪቱ አዲስ ተስፋና አማራጭ የመሆን ሰፊ ዕድል እንዳለው ጭምር ተነግሯል፡፡ ይህም ሁለቱ ተቋማት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ መነሻ እንደሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚቋቋመው ብሔራዊ ፌዴሬሽን ከመደራጀቱ በፊትም በስድስት ክልሎች ማለትም በሐረሪ፣ በድሬዳዋ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልላዊ ከተሞች የዒላማ ተኩስ ፌዴሬሽን እንደሚቋቋም ያስረዱት አቶ ታምራት፣ በቅርቡ በሌሎችም ክልሎችና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጭምር ሕጋዊ ሰውነት ኖሯቸው ስፖርቱ በመላ አገሪቱ እንዲስፋፋ ይደረጋል፡፡

እንደ አቶ ታምራት በአገሪቱ በተለይም በወታደራዊ ክፍሉ እየተዘወተረ ያለውን የዒላማ ተኩስ ውድድር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ይኖረው ዘንድ እንቅስቃሴው የተጀመረው ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ ነው፡፡

ስፖርቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ በተለይም ከኦሊምፒክ ስፖርቶች አንዱ ከሆነ ዓመታት ማስቆጠሩ ይታመናል፡፡ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ለዒላማ ተኩስ በወንዶች ዘጠኝ፣ በሴቶች ደግሞ ስድስት በድምሩ 15 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማዘጋጀት ውድድሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...