Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትአርክቲክ ተርኖች- ‹‹ከፍጥረታት የበለጠ የቀን ብርሃን የሚያዩት››

  አርክቲክ ተርኖች- ‹‹ከፍጥረታት የበለጠ የቀን ብርሃን የሚያዩት››

  ቀን:

  አርክቲክ ተርን የተባሉት ወፎች ከአርክቲክ አካባቢ ተነስተው እስከ አንታርክቲካ በሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጉዞ 35,200  ኪሎ ሜትር የሚያህል ርቀት ይበራሉ ተብሎ ይታመን ነበር። በቅርብ በተደረጉ ጥናቶች ግን ወፎቹ ከዚህ የበለጠ ርቀት እንደሚጓዙ መረጋገጡን በቁጥር 4 2017 ዕትሙ የዘገበው ጄደብሊው ዶትኦርግ ነው።

  ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት ጂዮሎኬተር የሚባሉ ትናንሽ መሣሪያዎች በበርካታ ወፎች ላይ ታሰሩ። እነዚህ ከእስክሪብቶ ክዳን ያነሰ ክብደት ያላቸው አስደናቂ መሣሪያዎች እንዳመለከቱት አንዳንድ ተርኖች ከአርክቲክ እስከ አንታርክቲካ ደርሶ መልስ በአማካይ 90,000 ኪሎ ሜትር ይበርራሉ፤ ይህም ማንኛውም እንስሳ ከሚያደርገው የፍልሰት ጉዞ ረጅሙ እንደሆነ ይታመናል። እንዲያውም አንዲት ወፍ 96,000 ኪሎ ሜትር ያህል በርራለች። ለመሆኑ የሚጓዙትን ርቀት በተመለከተ ቀደም ሲል በነበረው ግምታዊ አኃዝ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

  እነዚህ ወፎች ጉዟቸውን የሚጀምሩት ከየትኛውም ቦታ ቢሆን የሚበርሩት ጠመዝማዛ የሆነ አቅጣጫ ተከትለው ነው። ወፎቹ አብዛኛውን ጊዜ አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው የሚበርሩት የኤስ ቅርጽ ተከትለው ነው። ይህን የሚያደርጉትም ወፎቹ የሚበርሩት የነፋስን አቅጣጫ ተከትለው ስለሆነ ነው።

  ተርኖች 30 ዓመት ገደማ በሚሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከ2.4 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛሉ። ይህ ደግሞ ወደ ጨረቃ ሦስት ወይም አራት ጊዜ የደርሶ መልስ ጉዞ የማድረግ ያህል ነው! አንድ ተመራማሪ “ከ100 ግራም የማይበልጥ ክብደት ያላት ወፍ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ መቻሏ በጣም አስደናቂ ነው” ብሏል። ከዚህም በላይ አርክቲክ ተርኖች በሁለቱም ዋልታዎች ላይ የሚያሳልፉት የበጋ ወቅት በመሆኑ ላይፍ ኦን ኧርዝ፣  ናቹራል ሂስትሪ የተባለው መጽሐፍ ‹‹ከማንኛውም ፍጥረት የበለጠ የቀን ብርሃን ያያሉ›› ሲል ገልጿል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...