Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት‹‹ቃል በተግባር›› የክልሎች ጥያቄ

‹‹ቃል በተግባር›› የክልሎች ጥያቄ

ቀን:

 በየዓመቱ በሁሉም ክልሎች እየተዘዋወረ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዓመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ትላልቅ ስታዲየሞችን ማስገንባት በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ የመሠረተ ልማቱ አስፈላጊነት ባያጠያይቅም ከዚያ በፊት ቅድሚያ የሚፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ አሉ፡፡

የስታዲየሞቹን ፕሮጀክት በማከናወን ላይ ከሚገኙ ክልሎች መካከል ደግሞ ኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች ይጠቀሳሉ፡፡ አትሌቲክሱን ጨምሮ በርካታ ስፖርቶችን በክልሉ እያንቀሳቀሰ የሚገኘው የኦሮሚያ ክልል የጥሩነሽ ዲባባ የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል፣ የአምቦ ጎል ፕሮጀክትና ሌሎችም ማዕከላት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ክልሉ አሁን አሁን በተለይም በአትሌቲክሱ ቀደም ሲል የነበረውን ውጤት እያስጠበቀ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

በቅርቡ ወደ ኃላፊነት የመጣው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱ አመራር የመስክ ጉብኝት ካደረገባቸው ክልሎች የኦሮሚያ ክልል አንዱ ነበር፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም የክልሉ ስፖርት ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ስፖርት እየተዳከመ መምጣቱ በግልጽ ሲነገር ተደምጧል፡፡ ይህንኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ለብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው አመራሮች እንዳረጋገጡላቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት መሠረተ ልማት ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኪሮስ ሀብቴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርም ሆኑ ሌሎች የካቢኔ አባላት ክልሉ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሥራት እየተዳከመ የመጣውን የአትሌቲክስ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስፖርቶች ላይም ቀደም ብሎ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የጀመረው የመስክ ጉብኝት በአንድ ዙር ብቻ እንዳያበቃ፣ ይልቁንም የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች በበላይነት የሚመሩት ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይነት እንደሚኖረው ጭምር አቶ ኪሮስ ገልጸዋል፡፡ ከመስክ ጉብኝቱም ሁሉም ክልሎች ለመለስተኛ መሠረተ ልማቶችና ፕሮጀክቶች ትኩረት የሚሰጡ ስለመሆኑ ቃል መግባታቸውም አቶ ኪሮስ አስረድተዋል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ የመስክ ጉብኝት ካደረገባቸው ክልሎች ኢትዮጵያ ሱማሌ ይጠቀሳል፡፡ ክልሉ እንደ ሌሎች ክልሎች ሁሉ በሦስት የግንባታ ምዕራፍ የሚጠናቀቅ 60 ሺሕ ተመልካቾች ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ስታዲየም በ1.5 ቢሊዮን ብር በማስገንባት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የክልሉን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው እንዳስረዱት ከሆነ፣ ክልል ከአትሌቲክሱ ባሻገር በተለይ በእግር ኳስ እምቅ ችሎታና ብቃት ያላቸው ወጣቶች እንዳሉ፣ ይሁንና ከክልሉ ካቢኔ ጀምሮ ለስፖርቱ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ውጤቱም በዚያው ልክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወትሮ በተለየ አግባብ አብሮ ለመሥራት ያቀረበውን ይህን ሐሳብ ክልሉ በቀላሉ እንደማይመለከተው ያከሉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር፣ ካቢኔያቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በዚህ ሳይወሰን ሒደቱን በቅርበት መከታተል እንደሚኖርበት ጭምር ጠይቀዋል፡፡ ሌሎችም የካቢኔ አባላት ለተግባራዊነቱ ቃል ገብተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...