አስፈላጊ ግብዓቶች
ግማሽ ኪሎ ደበርጃን
ሩብ ኪሎ ፔፐሮኒ
1 በክብ ቅርጽ የተመተረ ቀይ ሽንኩርት
3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ኩባያ የተከተፈ ፐርሰሜሎ
ሩብ ኪሎ ቲማቲም
ሩብ ኩባያ የሚነሰነስ ፐርሰሜሎ
ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ዘይት ለመጥበሻ
አሠራር
- ደበርጃን በስሱ መትሮ ጨው በገባበት ውኃ ውስጥ ለግማሽ ሰዓት መዘፍዘፍ፤
- በንጹሕ ጨርቅ አድርቆ በፈላ ዘይት ውስጥ መጥበስ፣
- ፔፐሮኒውን በቁመት መትሮ ውኃውን አጥልሎ በጨርቅ ላይ ከደረቀ በኋላ በዘይት መጥበስ፤
- ለመጥበሻ ከዋለው ግማሽ ኩባያ ዘይት ድስት ውስጥ ጨምሮ ነጭና ቀይ ሽንኩርት እንደሁም ፐርሰሜሎ ቀላቅሎ መጥበስ፤
- በሌላ ድስት ውስጥ ከደበርጃኑ ትንሽ፣ ከፔፐሮኒው ትንሽ ከሥር አንጥፎ እላዩ ላይ የተጠበሰውን ሽንኩርት መጨመር፡፡ አስፈላጊ ከሆነም በክቡ የተመተረ ወይም የተፈጨ ቲማቲም ማድረግ፡፡ የቀረውን ደበርጃንና ፔፐሮኒ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ፐርሰሜሎ እላዩ ላይ መነስነስ፡፡ በክብ የተመተረ ቲማቲም እላዩ ላይ በመደርደር ትንሽ ዘይት አፍስሶ ምድጃ ውስጥ ወይም በፎርኔሎ ማብሰል፡፡
አራት ሰው ይመግባል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)