Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየብአዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ጠባቂ የነበሩት ግለሰብ ሞተው ተገኙ

የብአዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ጠባቂ የነበሩት ግለሰብ ሞተው ተገኙ

ቀን:

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዓለምነው መኮንን ዋና ጠባቂ የነበሩት አቶ አንዋር አህመድ ሞተው መገኘታቸው ታወቀ፡፡

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ መመርያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኘው ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአቶ ዓለምነው ዋና ጠባቂ የነበሩት አቶ አንዋር እሑድ ሰኔ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ሞተው ተገኝተዋል፡፡

ኮማንደር ዋለልኝ የአሟሟታቸውን ሁኔታ አስመልክተው ሲናገሩ፣ ‹‹እስካሁን በደረስንበት ደረጃ ራሱን እንዳጠፋ ነው ያረጋገጥነው፤›› ብለዋል፡፡ ራሳቸውን በምን ምክንያት ሊያጠፉ እንደቻሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ምክንያቱ ባለመታወቁ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹አልጋ ይዞ ካደረ በኋላ በራሱ ጥይት ነው የተመታው፤›› ብለው፣ አልጋ ለምን ይዘው እንዳደሩም ምክንያቱን ገና እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሟች አልጋ የያዙት ከቅዳሜ ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እንደነበር የገለጹት ኮማንደር ዋለልኝ፣ እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ ከጓደኞቻቸው ጋር በስልክ ሲነጋገሩ እንደነበር መረጃ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

‹‹ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ አልጋ የያዘው ሟች እሑድ ቀኑን ሙሉ የአልጋ ክፍሉ ተዘግቶ እንደዋለ፣ የሆቴሉ ባለቤቶችና ሠራተኞች ግራ ሲገባቸው አካባቢያቸው ወዳለው የፖሊስ ጣቢያ በማሳወቅ ፖሊስ ወደ ሥፍራው ሄዶ በመስኮት ሲገባ ሞቶ ተገኝቷል፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይዞት የነበረው ሽጉጥ ተተኩሶበታል፡፡ ከመሣሪያው አቀማመጥና ከልጁ ሞት አንፃር ሲታይ ራሱን እንዳጠፋ የሚያሳይ ነገር አግኝተናል፤›› ብለዋል፡፡

በራሳቸውን ሽጉጥ ራሳቸውን ካጠፉ የተኩስ ድምፅ የሆቴሉ ሠራተኞችና ባለቤቶች እንዴት አልሰሙም ተብለው የተጠየቁት ኮማንደሩ፣ ‹‹ሬሳው የተገኘው አድሮና ውሎ ነው፡፡ ምናልባት ጥይቱ የተተኮሰው ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት በኋላ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አልጋ ይዘው ከጎን ያደሩት ሰዎች በአካባቢው የጥይት ድምፅ አለመስማታቸውን ነግረውናል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

የአቶ ዓለምነው ዋና አጃቢ የነበሩት አቶ አንዋር ገና ወጣትና ትዳር ያልመሠረቱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ለሁለት ዓመታት ያህልም አቶ ዓለምነውን በጥበቃ እንዳገለገሉ ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 10 በሚገኘው ማረሚያ ቤት፣ አንድ እስረኛ ሊያመልጥ ሲል መያዙን ኮማንደር ዋለልኝ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት ለሕክምና ከማረሚያ ቤት፣ ወጥቶ የነበረው ግለሰብ ባገኘው አጋጣሚ ለማምለጥ ሲሞክር የጥበቃ ኃይሎች በመተኮሳቸው እንደተያዘ ተናግረዋል፡፡ ታራሚው በአስገድዶ መድፈር ሰባት ዓመት የተፈረደበት ታራሚ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ በታራሚው ላይ የተተኮሰው ጥይት አደጋ እንዳላደረሰበት ኮማንደሩ አክለው ገልጸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...