Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊብዥታን ያስከተለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ንብረት አወጋገድ ሥርዓት

ብዥታን ያስከተለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ንብረት አወጋገድ ሥርዓት

ቀን:

የፌዴራል በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ከውጪና ከኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ጋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክክር አድርጓል፡፡ ድርጅቶቹና ማኅበራቱ ለሁለት ቀናት በተወያዩበት ወቅት በዋናነት ትኩረት የተሰጠው የድርጅቶቹንና የማኅበራቱን ንብረቶች ለማስወገድና ለማስተላለፍ በተሻሻለው መመርያ ስድስት ላይ ነው፡፡

መመሪያውን አስመልክቶ በዕለቱ በተደረገው ገለጻ፣ ድርጅቶችና ማኅበራት ለረዥም ጊዜ የተገለገሉባቸው፣ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ወይም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉባቸውን ንብረቶች የማጣራት፣ የማስወገድና የማስተላለፍ ሥራ በአጣሪ ኮሚቴ መከናወን እንዳለበት የሚጠቁም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ይህ ዓይነቱ አቅጣጫ በብዙዎቹ ድርጅቶችና ማኅበራት ዘንድ ብዥታን ፈጥሯል፡፡ በምትኩም ሌሎች አማራጮች መፈለጉ የተሻለ ነው የሚል አስተያየትም ከተሰብሳቢዎች ተሰንዝሯል፡፡ በኮሚቴ ማሠራት ለጊዜ መጓተት መንስዔ ከመሆኑ ባሻገር፣ ለሙስና ይዳርጋል የሚል ሥጋት እንዳላቸው የጠቆሙ አስተያየት ሰጪዎችም ነበሩ፡፡

- Advertisement -

የተሻሻለው መመሪያ በንብረት ማጣራትና ማስወገድ ዙሪያ ከዚህ በፊት የነበረውን መጓተት በተጨባጭ ሊያስቀር የሚችል መሆኑን በምሳሌ ተደግፎ እንዲነገራቸው በኮሚቴ ከማከናወን ይልቅ ተቋማዊ በሆነ መልኩ ቢከናወን አይሻልም ወይ? ብለው የጠየቁ ታዳሚዎችም አልጠፉም፡፡

ኮሚቴ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን በአገር ደረጃም ብዙ ችግሮች እያስከተለ ነው፡፡ በሁሉም አካባቢ አንድ ችግር ሲፈጠር እስቲ በኮሚቴ ታይቶ ይጣራ ነው የሚባለው፡፡ ይህ ዓይነቱም አካሄድ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን በእውነት ውጤት እያስገኘ ነው ወይ? የኮሚቴውስ ተጠያቂነት ምን ያህል ነው? የሚለው እንዳልታየ፣ በተረፈ ንብረቶቹን በኃላፊነት ወስዶ በተጠያቂነት ሊሠራ የሚችል ተቋም መኖር እንደ አማራጭ መታየት እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል፡፡

መንግሥት የንብረት ግዢና ማስወገድ አገልግሎት እንዳለው ይህም አገልግሎት ደንብና መመሪያ እንዳወጣና በአጠቃላይ የመንግሥት ተቋማትም መመሪያውን መሠረት አድርገው ተገቢውን ሥራ እያከናወኑ እንደሆነ አንድ አስተያየት ሰጪ ገልጸው፣ ኤጀንሲውም ከዚህ ዓይነቱ አካሄድ ተሞክሮና ልምድ መቅሰም እንደሚኖርበት አስረድተዋል፡፡ ኤጀንሲውም ከድርጅቶችና ማኅበራት ጋር ተቀራርቦ የሚሠራበት አካሄድ ጎልቶ ሊታይ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኤጀንሲው የንብረት ማጣራት፣ ማስተላለፍና ማስወገድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኜ ሽብሩ ኮሚቴ የማቋቋሙ ሥራ የሚከናወነው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ወይም የማጣራቱ፣ የማስተላለፉና የማስወገዱ ሥራ ልዩ ሙያን የሚጠይቅ ሆኖ ከተገኘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የኤጀንሲው ቁልፍና መሠረታዊ ችግር የሰው ኃይሉ እየተመናመነ መምጣቱ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡  

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ መሠረት ገብረማርያም በበኩላቸው፣ የኮሚቴን ሥራ በልምድ ከማውገዝ ይልቅ ለሥራ አስተዋጽኦ ማድረጉ እንደ ዋነኛ ጠቀሜታ ተደርጎ መታየት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡

ከተሻሻለው መመርያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ የአጣሪው ኮሚቴ አባላት ከኤጀንሲው ሠራተኞች ወይም ንብረቱ ከሚጣራበት ድርጅት ወይም ማኅበር የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ወይም ለማጣራት አስፈላጊና አግባብነት ካላቸው የዘርፍና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ወይም መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ሊውጣጡ ይችላሉ፡፡ የአጣሪው ኮሚቴ አባላት እንደሚጣራው ንብረት፣ ብዛትና ስፋት እየታየ ቁጥራቸው ከሦስት እስከ አምስት ሊደርስ ይችላል፡፡ መመሪያው ከጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል፡፡             

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...