Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዋና ኦዲተር በአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እንዲያደርግ ታዘዘ

ዋና ኦዲተር በአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እንዲያደርግ ታዘዘ

ቀን:

  • ሳይገነቡ የተዘለሉ ብሎኮች ሁኔታ በኦዲቱ ይጣራል

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሒደቶች ላይ የኦዲት ምርመራ እንዲያከናውን፣ በፓርላማው መታዘዙና ምርመራውም መጀመሩ ታወቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት ጋር በመነጋገር በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ተጠሪነቱ ለፓርላማው የሆነውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር እንዳዘዙ ተመልክቷል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት የቤት ባለቤት ለመሆን የተመዘገቡ ነዋሪዎች ሀብት በመሆናቸው፣ ከንግድ ባንክ በሚገኝ በርካታ ቢሊዮኖች ብር ብድር የሚፈስበት ስለሆነ ግልጽነትን በዘርፉ ማስፈን ያስፈልጋል፡፡ የታለመውን ግብ ፕሮጀክቱ ማሳካት ያለበት በመሆኑ የኦዲት ምርመራው ታዟል ብለዋል፡፡

በከፍተኛና በጥልቅ የኦዲት ሥራ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በየዓመቱ ሲፈቀዱ የነበሩ በጀቶች፣ በሕጋዊ መንገድ ጥቅም ላይ መዋላቸው እንደሚጣራ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አስረድተዋል፡፡

የግንባታ ውል ከተፈረመ በኋላ የዲዛይን ለውጦች የተደረጉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታዎች በዲዛይን ለውጡ መሠረት የበጀት ክለሳ ተደርጎባቸዋል የሚለው፣ በኦዲቱ እንዲመለስ የሚፈለግ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ 

በተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ‹‹ጠፍተዋል›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የኮንዶሚኒየም ብሎኮች ጉዳይም በኦዲቱ ግልጽ የሆነ መልስ እንደሚያኝ ገልጸዋል፡፡

የግንባታ ግብዓቶች ግዢ ሕጋዊነትና የወጪዎቻቸው ይዘትም እንደሚመረመር ጠቁመው፣ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኦዲት ባለሙያዎች የምርመራ ሥራቸውን መጀመራቸውንም ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር መስፍን እንደገለጹት የኦዲት ምርመራው ጊዜ ሊወስድ የሚችል ስለሆነ፣ በቀጣዩ ዓመት አጋማሽ የኦዲት ግኝት ሪፖርቱ ለፓርላማ ሊቀርብ እንደሚችል ገምተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በፓርላማው በታዘዘው መሠረት በኢትዮጵያ ደረቅ ወደቦችና በጂቡቲ ወደብ የተከማቹ ገቢ ዕቃዎች የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከወጣባቸው በኋላ የማይነሱበትን ምክንያትና በኢኮኖሚው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመመርመር ላይ ይገኛል፡፡

በዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ የሚመራው የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ላለፉት ዓመታት ጠንካራ አፈጻጸም በማሳየት የፓርላማውን የክትትልና የቁጥጥር ተልዕኮ በመረጃ እየደገፈ ቢሆንም፣ ፓርላማው በሚቀርብለት መረጃዎች ላይ በመመሥረት ዕርምጃ ወደ መውሰድ ባለመግባቱ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ሙያዊ ድጋፍ ተስፋ በማሳጣት እንዳያስተጓጉለው ሥጋት አለ፡፡

በግንቦት ወር ሪፖርታቸውን ያቀረቡት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹም ዕርምጃ ባለመውሰዱ ብቻ የመንግሥት ተቋማት መታረም አለመቻላቸውን ለፓርላማው ገልጸው፣ ከዚህ በኋላ ይህ ዕርምጃ ያለመውሰድ ችግር ይቀረፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...