Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት የሎጂስቲክስ አሠራር ማሻሻያ ፕሮጀክት ሥራ ሊጀምር ነው

ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት የሎጂስቲክስ አሠራር ማሻሻያ ፕሮጀክት ሥራ ሊጀምር ነው

ቀን:

በዳዊት እንደሻው

መንግሥት የአገሪቱን የሎጂስቲክስ አሠራር ለመቀየር 32 ሚሊዮን ዶላር በጀት የመደበለትን የአንድ መስኮት ሥርዓት ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ ይህ ፕሮጀክት በአገሪቱ ገቢና ወጪ ንግድ የሚስተዋለውን ቀርፋፋ የሎጂስቲክስ ሥርዓት እንደሚያሻሽል ይጠበቃል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የአራት ዓመታት ዕድሜ ያለው ሲሆን፣ በሁለት የተለያዩ ደረጃዎች ይከናወናል፡፡ ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በሚገኝ ገንዘብ ይደገፋል፡፡

ፕሮጀክቱንም ለማስፈጸም መንግሥት የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ከሆነው ኮፒያ ጋር የኮንትራት ውል ተፈራርሟል፡፡

የአንድ መስኮት ሥርዓቱ የሚመለከታቸው ወደ አርባ የሚሆኑ ተቋማትን አሠራር በአንድ መረብ እንደሚያስተሳስር ተገልጿል፡፡

በተለይም ዕቃዎች ከውጭ አገር ሲገቡ ወይም ወደ ውጭ ሲወጡ የታክስና የቀረጥ፣ እንዲሁም አጠቃላይ የአሠራር ደረጃዎችን ያቀላጥፋል ተብሏል፡፡

በመጀመርያው ዙር ወደ 20 ከሚሆኑ ተቋማት ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ገቢዎችና ጉምሩክን ጨምሮ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሠራሮች እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

በቀጣዩ ዙር ደግሞ ቀሪዎቹ ተቋማት ወደ ሥርዓቱ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ ለዚህም ሥራ ሲባል በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፣ በዋናነት ሥራውን ከላይ ሆኖ ይመራል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለሥራው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንና ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑን፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ክትትል ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ደበሌ ቃበታ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለዚህ ሥራ ሲባል ራሱን የቻለ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት መቋቋሙን ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ለፕሮጀክት የትግበራ ዕቅድ ከአሁን በፊት የነበሩ አሠራሮች ወደፊት ምን መደረግ አለባቸው የሚለው ላይ ጥናቶች መደረጋቸውም ታውቋል፡፡ በአንድ መስኮት ሥርዓት ውስጥ ምን ምን ሥራዎች መካተት አለባቸው የሚለውም መለየቱ ተጠቁሟል፡፡

ከአሁን በኋላ አንድ የብሔራዊ ኮሚቴው ስብሰባ እንደሚኖር፣ ከዚያ በኋላ ግን ፕሮጀክቱ በግልጽ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያስፈልጉ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ግንባታ የሚሆኑ ዕቃዎች ግዢና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች በቅርቡ እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡

‹‹ይህ ፕሮጀክት የአገሪቱን አጠቃላይ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ይቀይራል ብለን እንጠብቃለን፤›› ሲሉ የኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አሠፋ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የአገሪቱ የሎጂስቲክስ ሥርዓት በብዙ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ፣ አሁንም ከብዙ የአፍሪካ አገሮች ወደኋላ የቀረ መሆኑ ይነገራል፡፡

ካሁን ቀደም በዓለም ባንክ በተጠና ጥናት እንደተመለከተው፣ አንድ የጉምሩክ ክሊራንስ ለማስጨረስ 103 ደረጃዎችንና 21 ዶክመንቶችን ማለፍና ማሟላት ይጠይቃል፡፡ ይህም የአገሪቷን የዕቃዎች ገቢና ወጪ ሥርዓት ቀርፋፋና ወደኋላ እንዲቀር አድርጎታል ነው የተባለው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...